አርእስተ ዜና
Sat. Nov 23rd, 2024

የሳኡዲ መንግስት ለኢትዮጵያ የዲጂታል ስነ ምህዳር እንደሚደግፍ አስታወቀ

የሳኡዲ መንግስት ለኢትዮጵያ የዲጂታል ስነ ምህዳር እንደሚደግፍ አስታወቀ
የሳኡዲ መንግስት ለኢትዮጵያ የዲጂታል ስነ ምህዳር እንደሚደግፍ አስታወቀ

ኢትዮጵያ ምቹ የዲጂታል ስነ ምህዳርን ለመፍጠር የጀመረችውን ስራ የሳኡዲ ዐረቢያ መንግስት እንደሚደግፍ አስታወቀ።

አለም አቀፉ የስራ ፈጠራ ምክር ቤት በሳዑዲ ዐረቢያ ሪያድ አውደ ጥናት አካሂዷል። በአውደ ጥናቱ የተሳተፉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ በሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ የጀመረችውን ምቹ የዲጂታል ስነ ምህዳር የመፍጠር ስራን የተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

እንደ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ከሆነ ሚኒስትር ዴኤታዋ ግዙፉን የነዳጅ ኩባንያ አራምኮን የነዳጅ ስርጭቱን የሚቆጣጠርበትን የዲጂታል አሰራር ጎብኝተዋል።
“ኩባንያው የነዳጅ ቁጥጥሩን ሙሉ ለሙሉ በዲጂታል አሰራር እየተገበረ ሲሆን ይህንን ልምድ ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት እናደርጋለን ብለዋል።”

በዚህ ወቅት የሳውዲ ዐረቢያ መንግስት ይህንን ምቹ የዲጂታል ስነ ምህዳር ፈጠራ ስራን እንደሚደግፍ ይፋ ማድረጋቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በሪያድ በተካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የተውጣጡ የመንግስት የቴክኖሎጂና የዘርፉ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

Related Post