አርእስተ ዜና
Sat. Nov 23rd, 2024

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሳፋሪኮም ጋር ኮንክሪት ተፈራረመ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሳፋሪኮም ጋር ኮንክሪት ተፈራረመ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሳፋሪኮም ጋር ኮንክሪት ተፈራረመ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና ሳፋሪኮም-ኢትዮጵያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የኮንክሪት ምሰሶ ኪራይ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላና የሳፋሪኮም-ኢትዮጵያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሚስተር አንዋር ሶውሳ ናቸው፡፡



በፌርማ ስነ-ስርዓቱ ወቅት ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ የተፈረመው የምሰሶ ኪራይ ስምምነት የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶችን ለቴሌኮም አገልግሎት ለመጠቀም የሚያስችል መሆኑን ገልፀው፤ መሰረተ-ልማቶችን በጋራ መጠቀም መቻሉ ጥራት ያለውና አስተማማኝ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል ብለዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም የኪራይ አገልግሎቱ በሃገሪቱ የተዘረጉ የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች በጋራ ለመጠቀም የሚያስችል ከመሆኑም በላይ የተቋሙን ገቢ ለማሳደግም ፋይዳው የጎላ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የሳፋሪኮም-ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈጻሚ አንዋር ሶውሳ በበኩላቸው ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር አብረው ለመስራት ዕድሉ በማግኘታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው፤ የተፈረመው የምሰሶ ኪራይ የሁለቱን ተቋማት ሃብት በጋራ ለመጠቀም የሚያስችልና ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የምሰሶ ኪራይ ስምምነቱ ዋና አላማ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተዘረጉ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት በተለይም ደግሞ የኮንክሪት ፖሎችን በጋራ ለመጠቀም የሚያስችል መሆኑን በፌርማ ስነ-ስርዓቱ ወቅት ተገልጿል፡፡

ስምምነቱ ተግባራዊ የሚደረገው በታላላቅ የሃገሪቱ ከተሞች ላይ በተተከሉ የኮንክሪት ምሰሶዎች ላይ ሲሆን፤ ውሉን የፈረመው ሳፋሪኮም በሚያገኘው አገልግሎት በዓመት 988 ብር ከ70 ሳንቲም ለአንድ ምሰሶ ኪራይ የሚከፍል መሆኑን ተመላክቷል፡፡



የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በተከላቸው የኮንክሪት ምሰሶዎች ኪራይ ተጨማሪ ገቢ ማግኘቱ በእርጅና ምክንያት የወደቁና የዘመሙ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን ማሻሻልና የመልሶ ግንባታ ስራ ማከናወን የሚያስችለው ይሆናል፡፡

በፊርማ ስነ-ስርዓቱ የሁለቱን ተቋማት ዋና ሥራ አስፈፃሚዎችን ጨምሮ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያና ሌሎች የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

Related Post