አርእስተ ዜና
Wed. Nov 13th, 2024

ኢትዮጵያና ጣሊያን የአንድ ሚሊዮን ዩሮ የእርዳታ ስምምነት ተፈራረሙ

ኢትዮጵያና ጣሊያን የአንድ ሚሊዮን ዩሮ የእርዳታ ስምምነት ተፈራረሙ
ኢትዮጵያና ጣሊያን የአንድ ሚሊዮን ዩሮ የእርዳታ ስምምነት ተፈራረሙ

ኢትዮጵያና ጣሊያን ለዜጎች መረጃ ምዝገባ አገልግሎት የሚውል የአንድ ሚሊዮን ዩሮ ( 56,967,900 ብር ) የእርዳታ ስምምነት በሂልተን ሆቴል ተፈራረሙ፡፡

የእርዳታ ስምምነቱን የፈረሙት በኢትዮጵያ መንግስት በኩል የገንዘብ ሚኒስትሩ ክቡር አቶ አህመድ ሺዴ ሲሆኑ በጣሊያን መንግስት በኩል ደግሞ የጣሊያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒትርና የጣሊያን አለም አቀፍ ትብብር ሀላፊ የተከበሩ ማሪያና ሴሬኒ ናቸው፡፡

በፊርማ ስነስርአቱ ወቅት ክቡር አቶ አህመድ ሺዴና የተከበሩ ማሪያና ሴሬኒ የሁለቱ ሀገሮች የልማት ትብብር ይበልጥ በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ በመግባባት መንፈስ ተወያይተዋል፡፡

Related Post