አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

የንግድ ድርጅት ለጊዜው ስለማሸግ

የንግድ ድርጅት ለጊዜው ስለማሸግ
የንግድ ድርጅት ለጊዜው ስለማሸግ

ማንኛውም ግብር ከፋይ በታክስ ህጉ መሰረት ግዴታውን ካልተወጣ አልያም የታክስ ህጉን ከጣሰ የንግድ ድርጅቱን እስከማሸግ ድረስ ሚያስቀጣ ህግ እንዳለ በታክስ ህጉ ተቀምጧል፡፡

በዚህም መሰረት፡-
1. አንድ ታክስ ከፋይ በተደደጋሚ፡-
ሀ. በግብር ህግ መሰረት የሚፈለግበትን ሰነድ ሳይዝ ሲቀር፣ ወይም
ለ. ታክሱን በመክፈያ ጊዜው ሳይከፍል ሲቀር የንግድ ድርጅቱ ለጊዜው እንዲታሸግ ይሆናል፡፡
2. ይህ ግዴታ ተፈፃሚ በሚሆንበት ጊዜ ታክስ ከፋዩ ማስጠንቀቂያ በደረሰው በ 7ቀናት ውስጥ የሚፈለግበትን ታክስ የማይከፍል ከሆነ ወይም የሚፈለግበትን ሰነድ ያልያዘ እንደሆነ ሚኒስቴሩ የታክስ ከፋዩን የንግድ ድርጅት ለ14 ቀናት በጊዜያዊነት የሚያሽግ መሆኑን የሚገልፅ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል፡፡

3. ታክስ ከፋዩ በተራ ቁጥር 2 በተሰጠው ማስጠንቀቂያ መሰረት ታክሱን ካልከፈለ ወይም የሚፈለግበትን ሰነድ ካልያዘ ሚኒስቴሩ የታክስ ከፋዩ የንግድ ድርጅት ከ14 ቀናት ላልበለጠ ጊዜ በከፊል ወይም በሙሉ እንዲታሸግ የሚያደርግ ትዕዛዝ (“የማሸጊያ ትእዛዝ” ተብሎ የሚጠቀስ) ይሰጣል፡፡
4. ሚኒስቴሩ ትዕዛዙን ተግባራዊ ለማድረግ ወደ ታክስ ከፋዩ የንግድ ድርጅት መግባት የሚችል ሲሆን የማሸጊያ ትዕዛዙ ተግባራዊ በሚደረግበት ጊዜ የፖሊስ መኮንን በቦታው እንዲገኝ ትዕዛዝ ሊሰጥ ይችላል፡፡

5. ሚኒስቴሩ በማሸጊያ ትዕዛዙ መሰረት በታሸገው የታክስ ከፋዩ ንግድ ድርጅት ህንፃ ላይ ፊት ለፊት በሚታይ ቦታ የሚከተሉትን ቃላት የያዘ ማስታወቂያ ይለጥፋል፡፡ “የታክስ ግዴታዎችን ባለመወጣቱ በፌደራል የታክስ አስተዳደር አዋጅ አንቀፅ 45
መሰረት በሚኒስቴሩ ትዕዛዝ ለጊዜው ታሽጓል”፡፡

6. ይህ እንዳለ ሆኖ ታክስ ከፋዩ የሚከተሉትን ሁኔታዎች አሟልቶ ከተገኘ ሚኒስቴሩ የታክስ ከፋዩን የንግድ ድርጅት እንደገና እንዲከፈት ያደርጋል፡፡
ሀ. ሥልጣን የተሰጠው አካል/ሰራተኛ ታክስ ከፋዩ የሂሳብ መዝገብ ሰነዶችን ለመያዝ የሚያስችል በቂ እርምጃ ወስዷል ብሎ ሲያምን፤
ለ. ታክስ ከፋዩ ታክሱን የሚከፍል ከሆነ፤

7. የማሸጊያ ትዕዛዝ የሚሰጠው በዋና ዳይሬክተሩ ወይም ደግሞ የማሸጊያ ትዕዛዝ ለመስጠት በልዩ ሁኔታ ሥልጣን በተሰጠው የታክስ ሠራተኛ ብቻ መሆኑ ተደንግጓል፡፡
ምንጭ የገቢዎች ሚኒስቴር

Related Post