አርእስተ ዜና
Sun. Jan 26th, 2025

ከአንድ ዓመት በላይ የሚሸፍን የኪራይ ክፍያ ግብር

ከአንድ ዓመት በላይ የሚሸፍን የኪራይ ክፍያ ግብር
ከአንድ ዓመት በላይ የሚሸፍን የኪራይ ክፍያ ግብር

አከራይ ወይም የተከራይ አከራይ ከአንድ ዓመት በላይ የሚሸፈን የቤት ኪራይ ገቢ የተቀበለ እንደሆነ አከራዩ ወይም የተከራይ አከራዩ በዚህ ዓይነት የተቀበለው ጠቅላላ የቤት ኪራይ ገቢ መጠን፣ ገቢውን በተቀበለበት የግብር ዓመት እንደተገኘ ተደርጎ ይቆጠራል፤ ሆኖም በዚህ የገቢ መጠን ላይ የሚከፈለው ግብር የቤት ኪራይ ገቢው የሚሸፍነው የግብር ዓመታት በማከፋፈል ይሰላል፡፡

ቤት በማከራየት የሚገኝ ጠቅላላ ገቢ የሚጨምራቸው ገቢዎች

1. የኪራይ ዋጋ ጭማሪን ወይም ተመሳሳይ ክፍያዎችን ጨምሮ በኪራይ ወል መሠረት ግብር ከፋዩ በግብር ዓመቱ የሚያገኘው ማናቸውም የገንዘብ መጠን፣
2. በኪራይ ውል መሠረት ተከራይ አከራዩን በመወከል በግብር ዓመቱ ለሌሎች የሚከፍላቸው ክፍያዎች፣
3. በቤቱ ላይ ለሚደርሰው ጉዳት ማስተካከያ ይሆን ዘንድ ግብር ከፋዩ የያዘውና በግብር ዓመቱ ያልተጠቀመበት ለግብር ከፋዩ ገቢ የተደረገው ማናቸውም ቦንድ፣ ዋስትና ወይም ተመሳሳይ የገንዘብ መጠን፣

4. ለግብር ከፋዩ ከሚከፈለው ኪራይ በተጨማሪ በኪራይ ውል መሠረት ተከራይ ራሱ ለቤቱ እድሳት ወይም ማሻሻያ የሚያወጣው ገንዘብ፣
5. ግብር ከፋዩ ቤቱን ያከራየው ከዕቃዎች ጋር በሚሆንበት ጊዜ ያገኘው ጠቅላላ ገቢ ከዕቃዎቹ የተገኘውን የኪራይ ገቢም ያጠቃልላል፡፡

Related Post