አርእስተ ዜና
Sat. Nov 23rd, 2024

1200 ኢትዮጵያዊያንን ከየመን ወደ አገራቸው ሊመለሱ ነዉ

1200 ኢትዮጵያዊያንን ከየመን ወደ አገራቸው ሊመለሱ ነዉ
1200 ኢትዮጵያዊያንን ከየመን ወደ አገራቸው ሊመለሱ ነዉ

ወደ አገራቸው ለመመለስ ላመለከቱ በቤሩት ለሚገኙ 180 ኢትዮጵያዊያን ቤሩት በሚገኘው የኢፌዲሪ ቆንስላ ጽ/ቤት አማካኝነት የሰነድ ማዘጋጅት ስራ መሰራቱን፤ በየመን የሚገኙ 1200 ኢትዮጵያዊያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ ከሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ክቡር አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አብራርተዋል

በሳኡዲ አረቢያ የሚኖሩ ዜጎቻቸን ደህንነት ለማስጠበቅ ከሳኡድ ንጉስ ጋር ውይይት መደረጉንና መብታቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ የሚያስችሉ ስራዎች መሰራታቸውን ክቡር አምባሳድር ዲና በመግለጫቸው አብራርተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ በቅርቡ ከነሐሴ 2 እስከ 4 ቀን 2012 ድረስ በጅቡቲ ጉብኝት በማድረግ ከአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ከሀገር ውስጥ ደህንነት ኃላፊ፣ ከፓሊስ ኮሚሽነር፣ ከኢጋድ ዋና ፀሐፊ፣ በጁቡቲ የአለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት ተወካይ እና የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ጋር ተገናኝተው በጁቡቲ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ባሉበት ሆነው ድጋፍ የሚያገኙበት ሁኔታ እንዲመቻች እንዲሁም የጅቡቲ መንግስት የዜጎቻችን አያያዝ መብት በጠበቀ ሁኔታ እንዲሆን ውይይት ማካሄዳቸውን፤ በተመሳሳይ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው የኢኮኖሚ ግንኙነት እንዲጠናከር ከጁቡቲ ንግድ ምክር ቤት ኃላፊዎች ጋርም ውይይት ማካሄዳቸውን አምባሳደር ዲና ገልጸዋል።

ከውጭ ተመላሽ ኢትዮጵያዊንን በዘላቂነት ለማቋቋም በኢትዮጵያ ከአለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት ሃላፊዎች ጋር እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርርብና በትብብር እየተሰራ መሆኑንም አምባሳደር ዲና አብራርተዋል።

Related Post