ከ1.64 ቢልዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ከፋፈም ገላልሼ የተሰራው የ55.4 ኪሎ ሜትር አስፋልት መንገድ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ።
ፕሮጀክትነቱ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ፕሮጀክት የሆነውና በቻይናው ሲሲሲሲ (CCCC) ስራ ተቋራጭ የተገነባው በሶማሌ ክልል ከፋፈም ገላለሼ የሚገኘው የ55.4 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ አገልግሎት መስጠት ጀመረ። በዛሬው እለት የሶማሊ ክልል ምክትል ርዕስ መስተዳድር ፅ/ቤት ም/ሀላፊ መሀመድ ዩሱፍ ሮብሌ እና ሌሎች አመራሮች የመንገዱን አሰራር እና የጥራት ደረጃውን ቦታው ላይ ተገኝተው የተመለከቱ ሲሆን ከቻይናው ሲሲሲሲ ስራ ተቋራጭ ወኪሎች ጋርም ውይይት አድርገዋል።
ከጉብኝቱ በኋላ ፕሮጀክቱ በተቀመጠለት የግዜ ገደብ በሶስት አመት ውስጥ መጠናቀቁን እና ጥራቱን በጠበቀ ሁኔታ መገንባቱ የገለፁት ምክትል ርዕስ መስተዳደር ፅ/ቤት ምክትል ቢሮ ሀላፊው አቶ መሀመድ ዩሱፍ ከዚህ ፕሮጀክት ሌሎች ስራ ተቋራጮች ልምድ በመውሰድ በክልሉ የተጀመሩ የመንገድ ስራዎችን በወቅቱ እና ጥራቱን በጠበቀ መልክ አንዲያጠናቅቁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ኃላፊው ከዚህ በተጨማሪ በቅርቡ ስራ የጀመረው ከገላልሼ ደጋህሚዶ የሚወስደው የ110 ኪሎ ሜትር የመንገድ ስራ ፕሮጀክት ጅምር እንቅስቃሴን የጎበኙ ሲሆን የሀገር በቀል ስራ ተቋራጭ የሆነው ቢአኤካ ኮንስትራክሽን ለአርብቶ አደሩ ህብረተሰብ ከብቶች መጠጥ አገልግሎት እንዲውል አስቦ በአጭር ግዜ ያዘጋጀውን የግድብ ውሃ ሙሌትም በቦታው ተገኝተው ጎብኝተዋል።
(ምንጭ = ሶማሊ ኮሙዮኒኬሽን)