አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

የወይቦ መስኖ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ 3,429 ሄክታር መሬት ያለማል ተባለ

የወይቦ መስኖ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ 3,429 ሄክታር መሬት ያለማል ተባለ
የወይቦ መስኖ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ 3,429 ሄክታር መሬት ያለማል ተባለ

በደቡብ ክልል የወላይታ ዞን በወይቦ ወንዝ ላይ በ2.44 ቢሊዮን ብር የሚገነባው የወይቦ መስኖ ልማት ፕሮጀክት ሕዳር 2014 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን ከ2-3 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ሲጠናቀቅ 3,429 ሄክታር መሬት የማልማት አቅም አለው፡፡

ፕሮጀክቱ የሚገነባው በወላይታ ዞን በቦሎሶ ሶሬ ወረዳና በቦሎሶ ቦምቤ ወረዳዎች ውስጥ ነው፡፡ ሲጠናቀቅ በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ 4 ቀበሌዎችና በቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ 7 ቀበሌዎች ውስጥ የሚገኙ ከ12,000 በላይ አርሶ አደሮችን በቀጥታና በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡



የወይቦ መስኖ ልማት ፕሮጀክት የግድቡ ርዝመት 660 ሜትርና የግድቡ ከፍታ 32.7 ሜትር ሲሆን 630 ሄክታር ላይ ውሃው ወደ ኃላ የሚተኛ ሆኖ ፕሮጀክቱ ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ 60 ሚሊዮን ሜትር ኩብ ውሃ የመያዝ አቅም አለው:: ከግብርናም በተጨማር ለቱሪስት መስህብነትና ለዓሳ ምርት ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በሁለት ሎቶች ተከፍሎ የሚገነባ ሲሆን ሎት-1 (የግድብና ተያያዥ ሥራዎች ግንባታ) በደቡብ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት እንዲሁም ሎት-2 (የመስኖ መሬት ዝግጅት ግንባታ) የሚገነባው ክሮስ ላንድ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ጋር በጆይንት ቬንቸር በመቀናጀት ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ተቆጣጣሪ መኃንዲስ የደቡብ ዲዛይንና ቁጥጥር ኢንተርፕራይዝ ነው፡፡ ህዳር ወር ላይ የተጀመረዉ ፕሮጀክት በየካቲት ወር 2014 ዓ/ም ድረስ ሎት -I 1.39% ሎት -II 3.48 % መከናወኑን የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ጠቁሟል፡፡


Related Post