አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

የኢትዮጵያ ግብርና አፈፃፀም ላይ ግምገማ ተካሄደ

የኢትዮጵያ ግብርና አፈፃፀም ላይ ግምገማ ተካሄደ
የኢትዮጵያ ግብርና አፈፃፀም ላይ ግምገማ ተካሄደ

በግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት እየተተገበረ ያለው የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን ክላስተር ፕሮግራም /ገበያ ተኮር ኩታ-ገጠም እርሻ የ2015 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም እና የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ግምገማ የባለድርሻ አካላት ተወካዮች በተገኙበት ተካሄደ፡፡

የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) መድረኩን ሲከፍቱ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት እና የልማት አጋር ድርጅቶች ገበያ ተኮር ኩታ-ገጠም እርሻን እያስፋፉ መሆኑን ገልፀው፤ መንግስትን ለመደገፍ እየተሰሩ ያለውን ስራ አድንቀዋል፡፡

የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር) የመድረኩን ዓላማ ሲገልፁ የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን ክላስተር ፕሮግራም (ACC) የ2015 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም እና የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድን በመገምገም ከባለድርሻ አካላት ለቀጣይ ስራ አስፈላጊ ግብዓትን ለማግኘት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን ክላስተር ፕሮግራም የ2015 በጀት ዓመት አጠቃላይ የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ፤ እንዲሁም ትግራይ ክልል በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን ክላስተር ስራ (ACC) እንዲቀጥል በቅርቡ ለክልሉ የተደረገውን ድጋፍ የተመለከተ ሪፖርትም ቀርቦ ውይይት ተደርጎል፡፡

በመጨረሻም ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ከተሳታፊዎች ለተነሱላቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች ማብራሪያ ሰጥተው፤ ለባለድረሻ አካላት ቀጣይ የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡ የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን ክላስተር ፕሮግራም (ACC) በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በትግራይ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች እና በሲዳማ ክልሎች በ300 ወረዳዎች ላይ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡

Related Post