አርእስተ ዜና
Wed. Nov 13th, 2024

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን ውጤታማ ለማድረግ ምክር ቤት ተቋቋመ

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን ውጤታማ ለማድረግ ምክር ቤት ተቋቋመ
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን ውጤታማ ለማድረግ ምክር ቤት ተቋቋመ

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን ተግባራዊና ውጤታማ ለማድረግ 22 ባለድርሻ አካላት የተካተቱበት ምክር ቤት ተቋቁሟል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሺሰማ ገብረስላሴ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ ንቅናቄው ውጤታማ እንዲሆን ለዘርፉ ማነቆ የነበሩትን ችግሮች መቅረፍ የሚቻልባቸው ስራዎች እየተሰሩ ናቸው ብለዋል።

በዚህም ከስራ የወጡ ኢንዱስትሪዎች ችግሮቻቸውን ቀርፎ ዳግም ወደ ስራ ከመመለስ ጀምሮ ኢንዱስትሪዎች በሙሉ አቅማቸው ማምረት እንዲችሉ እድል ይፈጠራል፤ አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን የመሳብና ምቹ ሁኔታን የመፍጠር ስራም ይሰራል ነው ያሉት።

ኢንዱስትሪዎቹ የግብአት፣ የጥሬ እቃ፣ የብድርና የውጭ ምንዛሬ እንዲሁም የመስሪያ ቦታና መሰል ጥያቄዎቻቸውን በአፋጣኝ የሚመልስና መመለሱንም ማረጋገጥ የምክር ቤቱ ሃላፊነት ነው ተብሏል።

ሚኒስትር ዴኤታው እንዳሉት ንቅናቄው ከ10 አመቱ የልማት እቅድ ጋር ተዛምዶ የሚተገበር ሲሆን ለተግባራዊነቱና ለውጤታማነቱም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሃላፊነታቸውን በብቃት እንዲወጡም ጠይቀዋል።
ምንጭ፡- ፋና

Related Post