አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

ክሮሽያ ኤምባሲዋን በኢትዮጵያ ለመክፈት ማቀዷን ገለጸች

ክሮሽያ ኤምባሲዋን በኢትዮጵያ ለመክፈት ማቀዷን ገለጸች
ክሮሽያ ኤምባሲዋን በኢትዮጵያ ለመክፈት ማቀዷን ገለጸች

አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ከክሮሽያ የፖለቲካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል ፒታር ማሃቶብ ጋር በኢትዮጵያና ክሮኤሽያ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር የሚያስችል ውይይት አካሂደዋል።

በወቅቱም ዳይሬክተር ጄኔራሉ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በማለም ኤምባሲዋን በኢትዮጵያ ለመክፈት ማቀዷን ገልጸዋል። በውይይታቸውም በሀገራቱ መካከል ያለውን ግንኙነት ከፍ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንዲሁም በባለዙ ወገን መድረኮች ያለቸውን ትብብር አጠናክሮ ለማስቀጠል ከመግባባት ላይ ደርሰዋል።

በተያያዘ ዜና አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ከክሮሽያ የኢኮኖሚና ልማት ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል ኢቫን ዚኮቪች ጋር በኢትዮጵያና ክሮሽያ የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ማጠናከር የሚያስችል ምክክር አካሂደዋል።

አምባሳደር ደሚቱ በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ መንግስት ኢኮኖሚውን ለማሳደግና የኢንቨስትመንት መስኮችን ምቹ ለማድርግ እያከናወናቸው ስለሚገኙ ተግባራት አብራርተዋል።

ኢቫን ዚኮቪች በበኩላቸው የመንግስትን ተግባር አድንቀው የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነትና ልማት ለማሳደግ እንቅስቃሴ እንደሚደረግ ተናግረዋል። የክሮሽያ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት መስክ እንዲሳተፉ የሚያስችል ስራ መንግስታቸው እንደሚያበረታታ ዳይሬተር ጄነራሏ ገልፀዋል።

Related Post