አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

ከጫት በአመት በአማካኝ 56 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኝቷል

ከጫት በአመት በአማካኝ 56 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኝቷል
ከጫት በአመት በአማካኝ 56 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኝቷል

ከጫት የወጪ ንግድ ከ2010-2014 በጀት ዓመት በአማካኝ በአመት 56.353 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ኢትዮጵያ ማግኘቷን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር አስታወቀ።

ጫት የወጪ ንግድ ዘርፍ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፍታት ከዘርፉ የሚገኘውን የውጪ ምንዛሪ ገቢ ለማሳደግ ከጫት ላኪዎች ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡
ሀገራችን የውጪ ምንዛሪ ገቢ ለማግኘት ለውጪ ገበያ ከምታቀርባቸው ምርቶች ውስጥ ጫት አንዱ ነው፡፡ የዘርፉ ወጪ ንግድ በርካታ ችግሮች ያሉበት በመሆኑ ሀገሪቱ ማግኘት የሚገባትን ገቢ እያገኘች አይደለም፡፡

ችግሮቹ ላይ በመምከር እና መፍትሄ በማበጀት ሀገራችን ከጫት ወጪ ንግድ የምታገኘውን የውጪ ምንዛሪ ለማሳደግ በዛሬው እለት ከጫት ላኪዎች ጋር በድሬዳዋ ከተማ ወይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ውይይቱ የተዘጋጀው በዘርፉ ልማት እድሎችና ችግሮች ላይ በ2014 በጀት ዓመት በጫት ወጪ ንግድ የተሻለ የውጪ ምንዛሪ ገቢ ካስገኙ የጫት ላኪዎች ጋር በመወያየት ዘርፉን ካሉበት ማነቆ ለማላቀቅ መሆኑን የንግድ ትስስርና የወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ውይይቱን በንግግር በከፈቱበት ወቅት ገልጸዋል፡፡

Related Post