አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

ኢትዮጵያ የቱሪዝም ሀብቷን በእስራኤል አስተዋወቀች

በእስራኤል በየዓመቱ የሚካሄደው የቱሪዝም ጉባኤና ዐውደ ርዕይ በዚህ ዓመት “ዓለም አቀፍ የሜዲትራኒያን የቱሪዝም ገበያ 2022” በሚል ርዕስ ትናንት የተጀመረ ሲሆን ከመጋቢት 20~21 ቀን 2014 ዓ.ም ይቆያል።

በጉባዔው መክፈቻ የእስራኤል ፕሬዚዳንት ሚር አይዛክ ሄርዞግ፣ የእስራኤል የቱሪዝም ሚኒስትር እና ሌሎች ባለሥልጣናትና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ከተለያዩ አገራት የመጡ የመንግስታት ተወካዮች በዘርፉ የተሰማሩ አካላትና ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን፣ ዐውደ ርዕዩ ቱሪዝም ሕዝቦችን ለማቀራረብ ትልቅ ፋይዳ ያለው መሆኑ ተገልጿል።



በዚህ ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ዐውደ ርዕይ ላይ ብዙ አገሮች በቱሪዝም ያላቸውን መስህብ ለተሳታፊዎች በምስል የተደገፈ ዝግጅት ቀርቧል። በዐውደ ርዕዮ ኢምባሲያችን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመሆን፣ ኢትዮጵያ ምድረ ቀደምት መሆኗን፣ አገራችን ባህላዊ ቅርሶችን፣ የታሪክ ሃብት እና የማራኪ ብዝሀነቷ ነጸብራቅ የሆኑ የዓለም ድንቅ ስፍራዎችን እና የማይዳሰሱ ቅርሶችን በማሳየት በምስል በገለጻ ተደርጓል።

በእስራኤል የኢፌዲሪ ኢምባሲም መንግስት ለመስኩ የሰጠውን ትኩረት በሚመለከት ገለጻ በማቅረብ፣ በአውደ ርዕይ ለሚሳተፉ ኢትዮጵያን መጎብኘት ለሚፈልጉ እስራኤላውያን፣ እንዲሁም አስጎብኚዎች አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን በማሳወቅ ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ ጥሪ አቅርቧል።


Related Post