አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

ኢትዮጵያ ለጎብኚዎች አንድ ተጨማሪ የቱሪዝም ምርት ጨመረች

ኢትዮጵያ ለጎብኚዎች አንድ ተጨማሪ የቱሪዝም ምርት ጨመረች
ኢትዮጵያ ለጎብኚዎች አንድ ተጨማሪ የቱሪዝም ምርት ጨመረች

በዚህ ሳምንት ማክሰኞ ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለጎብኚዎች አንድ ተጨማሪ የቱሪዝም ምርት የሆነዉን የሳይንስ ሙዚየምን መርቀው ከፍተዋል።

በ6.78 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ሙዚየሙ ሁለት ግዙፍ ህንጻዎች አሉት። በሙዚየሙ ውስጥ ቋሚ እና ጊዜያዊ አውደ ርዕይ ማሳያዎች አሉት።
ሙዚየሙ ሳይንስ ጥበባዊ በሆነ መንገድ የሚገለጽበት ጥበብም ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሚታይበት ነው ተብሏል።

ከተፈጥሮ ስርዓት ጋር ተስማሚ ሆኖ የተገነባው ሙዚየሙ ከጸሐይ ብርሀን የኤኤሌክትሪክ ሀይል የሚያገኝ ሲሆን የሙዚየሙ ውጫዊ ክፍል የቀለበት እና የጉልላት ቅርጽ እንዲኖረው ተደርጎ የተገነባ በመሆኑ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ቱሪስት የመሳብ ዕድል ይኖረዋል፡፡

Related Post