አርእስተ ዜና
Sat. Nov 23rd, 2024

ኢትዮጵያና ጅቡቲ በጋራ የጅቡቲ ወደብ ስራን እንዲመሩ ተጠየቀ

ኢትዮጵያና ጅቡቲ በጋራ የጅቡቲ ወደብ ስራን እንዲመሩ ተጠየቀ
ኢትዮጵያና ጅቡቲ በጋራ የጅቡቲ ወደብ ስራን እንዲመሩ ተጠየቀ

በወጪና ገቢ ንግድ የተሰማሩ ባለሃብቶችና ሸቀጦችን የሚያጓጉዙ ሹፎሮች በጅቡቲ ወደብ እያጋጠማቸዉ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት የኢትዮያና የጅቡቲ መንግስት በጋራ የጅቡቲ ወደብ ስራን እንዲመሩ ጥሪ ቀረበ፡፡

ላለፉት አስራ አምስት አመታት የገቢና የወጪ እቃዎችን ወደ ጁቡቲ ወደብና ከወደቡ ወደ መሃል ሀገር ሲያጓጉዝ የነበረዉ የግዜ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ግዜሽወርቅ ተሰማ የኢትዮጵያ መንግስት ለችግሮቹ ትኩረት ሰጥቶ ከጅቡቲ መንግስት ጋር እንዲደራደር መክረዋል፡፡

ኢትዮጵያዉያን የከባድ መኪና ሹፌሮች ‘ፒካዶስ’ በሚባለዉ የጅቡቲ ድንበር እያጋጠማቸዉ ያለዉን የምግብና የመኝታ ስፍራ ችግር የከፋ መሆኑን ወ/ሮ ግዜሽወርቅ ይናገራሉ፡፡በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግስት በሎጅስቲክ የስራ መስክ የተሰማሩትን የሃገር ዉስጥ ኩባንያዎች ደግፎ በማሳደግ ፋንታ ለዉጭ ባለሃብቶች ትኩረት መስጠቱ ትክክል እንዳልሆነም አብራርተዋል፡፡

ኡትዮጵያ የኤርትራን አሰብ ወደብ መጠቀም ካቆመችበት እ.ኤ.አ 1998 አ.ም ጀምሮ የጂቡቲ ወደብ ብቸኛዉ የኢትዮጵያ የወጪና የገቢ ንግድ መስመር በመሆን በመገልገል ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡የኢትዮጵያ መንግስት ለጅቡቲ ወደብ አገልግሎት እስከ 2 ቡሊዮን ዶላር በአመት እንደሚከፍል መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
[embedyt] https://www.youtube.com/watch?v=FKlccbo80jU[/embedyt]

Related Post