አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

ኢትዮጵያና ስሎቬኒያ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ሊያጠናክሩ ነው

ኢትዮጵያና ስሎቬኒያ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ሊያጠናክሩ ነው
ኢትዮጵያና ስሎቬኒያ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ሊያጠናክሩ ነው

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ከተመራው የስሎቬኒያ ልኡካን ጋር በቢሯቸው ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ኢትዮጵያ በቱሪዝም፣ በአገልግሎት እና በኢኮኖሚ ዘርፍ ያልተነካ እምቅ አቅም ያላት በመሆኑ የሁለቱን ሀገራት ሁለትዮሽ የንግድ ግንኙነት ማጠናከር እንደሚገባ አቶ ገብረመስቀል ገልጸዋል፡፡ ላለፉት አምስት አመታት ኢትየጵያ በሁለንተናዊ ዘርፍ በለውጥ ሂደት ውስጥ መሆኗን የጠቀሱት ሚኒስትሩ ከአለም ሁኔታ ጋር በማጣጣም እየሰራች ስለሆነ ስሎቬኒያ በቴክኖሎጅ፣ በጥናትና ምርምር እና በኬሚካል ኢንዱስትሪ ያላትን አቅም በመጠቀም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከርና ለማሳደግ ይሰራልም ብለዋል፡፡

የስሎቬኒያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትርና የአውሮፓ ጉዳዮች ሚኒስትር ወ/ሮ ታንጃ ፋጆን የኢትዮጵያና የስሎቬኒያ የንግድ ግንኙነት መሻሻል አለበት ያሉ ሲሆን በኢትዮጵያ ቆይታችን የጋራ የሚያደርጉንን እድሎች በመጎብኘትና በመረዳት በቀጣይ ሁለትዮሽ ግንኙነትን በሚያሳድጉ እና የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጡ ጉዳዮች ሁሉ አብረን እንሰራለን ብለዋል፡፡

በውይይቱ ላይ በጣሊያን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አንባሳደር ወ/ሮ ደሚቱ ሀምቢሳ የተገኙ ሲሆን ኢትዮጵያ በዩኔስኮ ያስመዘገበቻቸውና አዳዲስ እየተገነቡ ያሉ የቱሪስት መዳረሻዎች ለልኡካኑ ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን የኢትዮጵያ የቡና አፈላል ሥነ-ሥርዓት በተግባር የተደገፈ ገለፃ ተደርጎ አድናቆታቸውን ቸረዋል፡፡

Related Post