አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

ቡና ባንክ 1 ነጥብ 35 ቢሊየን ብር ማትረፋን አስታወቀ

ቡና ባንክ 1 ነጥብ 35 ቢሊየን ብር ማትረፋን አስታወቀ
ቡና ባንክ 1 ነጥብ 35 ቢሊየን ብር ማትረፋን አስታወቀ

ቡና ባንክ በበጀት አመቱ መጨረሻ ከግብር በፊት 1 ነጥብ 35 ቢሊየን ትርፍ ማግኘቱን አስታውቋል።

ባንኩ ይሄን ያስታወቀው በአዲስ ፓርክ ሚሊኒየም አዳራሽ በተካሄደው ዓመታዊው የባለአክስዮኖች 14ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን በዛሬው ዕለት ህዳር 30 2016 ባካሄደበት ወቅት ነው። በቀረበው ሪፓርት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ሰኔ 30 2023 በተጠናቀቀው በጀት ዓመት፤ የተቀማጭ ገንዘብ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በ9 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ማሳደግ መቻሉን የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አለማየሁ ሰዋገኝ ገልጸዋል።

የተቀማጭ ገንዘብ መጠን በ34 ነጥብ 6 በመቶ ከፍ በማድረግ 36 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር መድረሱን አመላክተዋል። እንዲሁም ባንኩ ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች በዓመቱ በአጠቃላይ 8 ነጥብ 92 ቢሊየን ብር ማበደሩን ጠቁመዋል ።

በተጨማሪም በበጀት አመቱ ለማህበራዊ ድጋፍ፣ ለአካባቢ ተኮር ፕሮጀክቶችና ለሌሎች ግብረ ሰናይ ተግባራት 41 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ድጋፍ በማድረግ ማህበራዊ ሃላፊነቱን መወጣቱ ገልጸዋል።

በአንፃሩ ዓለምአቀፋዊና ሃገራዊ ችግሮች ባስከተሉት ተጽዕኖ ከውጭ አገር የሚላክ ሀዋላ እንዲሁም የኤክስፖርት ስራ ጉልህ በሆነ መልኩ መቀዛቀዙ፤ በውጭ ምንዛሬ ግኝት በኩል የባንኩን አፈፃፀም በታቀደው ልክ እንዳይከወን አሉታዊ ጫና ማሳደሩን ገልጸዋል። ከተመሰረተ 14 ዓመታትን ያስቆጠረው ቡና ባንክ ከ13 ሺህ በላይ ባለአክሲዮኖችና ከ4 ሺህ በላይ ሰራተኞች ያሉት ሲሆን 465 ቅርንጫፎችም አሉት።

Related Post