አርእስተ ዜና
Thu. Dec 26th, 2024

በጋምቤላ ያልታወቁ ታጣቂዎች ጥቃት አደረሱ

በጋምቤላ ያልታወቁ ታጣቂዎች ጥቃት አደረሱ
በጋምቤላ ያልታወቁ ታጣቂዎች ጥቃት አደረሱ

በጋምቤላ ክልል ከጂካዎ ወረዳ ወደ መተሀር በመጓዝ ላይ ባለ የሞተር ጀልባ ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት አንድ ሰው ገድለው ስድስት ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ ማድረሳቸውን የክልሉ መንግስት አስታወቀ።

ከቆሰሉት ሰዎች መካከል ሁለቱ ወደ ጋምቤላ ሆስፒታል ሪፈር ተደርጎላቸው ህክምናቸውን እየተከታተሉ ሲሆን አራቱ በኝንኛንግ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል። ከጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት (መስከረም 12/2015) ዓ.ም የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኡገቱ አዲንግ እንዳሉት ትናንት ምሽት 1 ሰዓት ከ 45 አካባቢ መነሻቸውን ከጂካዎ ዲልድይ አድርገው ወደ መተሀር በመጓዝ ላይ ባሉ ሰዎች ላይ ከደቡብ ሱዳን ማሉዋል ጋኦት በሚባል ቦታ ላይ ተኩስ ተከፍቷል ብለዋል።

በተከፈተው ተኩስ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ ስድስት ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ መድረሱን አመልክተዋል። የመቁሰል አደጋ ከደረሰባቸው መካከል ሁለቱ ላይ ከባድ አደጋ በመድረሱ በጋምቤላ ሆስፒታል ህክምናቸውን እየተከታተሉ ሲሆን አራቱ በኝንኛንግ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ህክምና ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።

አቶ ኡገቱ አክለውም ከተሳፋሪዎቹ መካከል ሶስት ሰዎች የደረሱበት ያልታወቀ መሆኑን ጠቁመው መንግስት ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ አስረድተዋል። መንግስት ጥቃት አድራሾችን ለይቶ ለመያዝ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ አቶ ኡገቱ አመልክተዋል።

Related Post