አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

በገንዘብ ሚኒስቴር እና በገቢዎች ሚኒስቴር መካከል ስምምነት ተደረገ

በገንዘብ ሚኒስቴር እና በገቢዎች ሚኒስቴር መካከል ስምምነት ተደረገ
በገንዘብ ሚኒስቴር እና በገቢዎች ሚኒስቴር መካከል ስምምነት ተደረገ

ኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስቴር እና በገቢዎች ሚኒስቴር መካከል የታክስ ፖሊሲና አስተዳደር ጉዳዮችን በቅንጅት ለማከናወን የፕሮቶኮል ስምምነት ተከናውኗል።

የፕሮቶኮል ስምምነቱን የፈረሙት የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ እና የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ ናቸው። በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ የታክስ ፖሊሲ እና የታክስ አስተዳደር ጉዳዮች ተጣጥመው እና በተቀናጀ አኳኋን እንዲመሩ ማድረግ መንግሥት በታክስ አማካኝነት የሚያስፈፅማቸውን የኢኮኖሚ አጀንዳዎች ከግብ ለማድረስ እንዲሁም ለልማት ሥራዎች ማስፈፀሚያ የሚያስፈልገውን ገቢ በብቃት ለመሰብሰብ ወሳኝ በመሆኑ የፕሮቶኮል ስምምነቱ አስፈልጓል ብለዋል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ በበኩላቸው ስምምነቱ ያስፈለገው የታክስ ፖሊሲን የሚያመነጨውና አፈፃፀሙን የሚከታተለው የገንዘብ ሚኒስቴር እንዲሁም የታክስ አስተዳደሩን የሚመራው የገቢዎች ሚኒስቴሩ ባለሙያዎች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ እና ሥራቸውን በቅንጅት እንዲመሩ ለማድረግ የሚያስችል የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት ነው ብለዋል።

Related Post