አርእስተ ዜና
Fri. Nov 22nd, 2024

በቴሌብር የተከናወነ የነዳጅ ግብይት 100 ሚሊዩን ብር አለፈ!

በቴሌብር የተከናወነ የነዳጅ ግብይት 100 ሚሊዩን ብር አለፈ!
በቴሌብር የተከናወነ የነዳጅ ግብይት 100 ሚሊዩን ብር አለፈ!

ከ16 ቀናት በፊት የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ትግበራን ተከትሎ የተጀመረው ነዳጅን በቴሌብር የመገበያየት አሰራር ከ101ሺ በላይ በተደረገ የግብይት መጠን 14 ሚሊየን ብር ድጎማን ለአሽከርካሪዎች መፈጸም አስችሏል።

ይህን አስመልክቶ የኩባንያችን ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬሕይት ታምሩ ለሚዲያው ማህበረሰብ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን 26,849 ተሽከርካሪዎች በድጎማው ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን እና 609 ማደያዎች ግብይት መፈጸም መጀመራቸው ተገልጿል። በ16ቱ ቀናት ውስጥ ምንም ያጋጠመ የጎላ ችግር አለመኖሩን ገልጸው ሲስተሙ መረጃውን በሚፈለጉ መለኪያዎች በማንኛው ሰዓት ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ማቅረብ የሚያስችል ሲሆን አፈጻጸሙም የሚያበረታታ መሆኑ ተብራርቷል።

በመቀጠልም ከማኔጅመንት አባላት ጋር በመሆን በተመረጡ ነዳጅ ማደያዎች በመገኘት በቴሌብር እየተከናወነ የሚገኘውን የነዳጅ ክፍያ ስርዓት አፈጻጸም የጎበኙ ሲሆን በጉብኝቱ ወቅት አሽከርካሪዎች እና የማደያዎቹ ሰራተኞች ስለትግበራው አበረታች አስተያቶችን እና ግብአቶችን ሰጥተዋል።

ለትግበራው ከ2500 በላይ ሰራተኞች ድጋፍ በማድረግ ስራ ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙና ይህም የትግበራውን አፈጻጸም የተሻለ እንዲሆን እንዳገዘውም ተመላክቷል።
ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ በሆነው የዘመናችን የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ቴሌብር በቀጣይም በተመሳሳይ መልኩ የማህበረሰባችንን የእለት ተእለት ህይወት በማቅለል፣ የዲጂታል ኢትዮጵያን ራዕይ ዕውን የማድረጉን ተግባር አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል፡፡

Related Post