አርእስተ ዜና
Thu. Dec 26th, 2024

ምክር ቤቱ ሶስት የብድር ስምምነቶችን መርምሮ አፀደቀ

ምክር ቤቱ ሶስት የብድር ስምምነቶችን መርምሮ አፀደቀ
ምክር ቤቱ ሶስት የብድር ስምምነቶችን መርምሮ አፀደቀ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ አመት የስራ ዘመን ባካሄደው 4ኛ አስቸኳይ ስብሰባው ሶስት የብድር ስምምነቶችን መርምሮ አጸደቀ፡፡

ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በኮሪያ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ መካከል ለኮሮና ቫይረስ አስቸኳይ ጊዜ ምላሽ የበጀት ድጋፍ ፕሮግራምና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች አቅርቦት ማስፈፀሚያ የተደረጉትን ሁለት የብድር ስምምነት ረቂቅ አዋጆች መርምሮ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

የብድር ስምምነቶቹ የገንዘብ መጠንም ለኮሮና ቫይረስ አስቸኳይ ጊዜ ምላሽ የበጀት ድጋፍ 40 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እና ለህክምና መገልገያ መሳሪያዎች አቅርቦት ማስፈፀሚያ 30 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ሲሆን የሁለቱም ስምምነት የብድር አከፋፈል ስርዓት የ15 አመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ40 አመታት ጊዜ ውስጥ ተከፍሎ የሚጠናቀቅ መሆኑ ታውቋል፡፡

ምክር ቤቱ በውሎው በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በዳንሴክ ባንክ ኤ.ስ መካከል ለአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማፅደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅንም መርምሮ ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1227/2013 በማድረግ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

የተፈረመው የብድር ስምምነትም 117 ሚሊዮን 300 ሺህ /አንድ መቶ አስራ ሰባት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሺህ/ ዩሮ ሲሆን የአምስት አመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ20 አመታት ውስጥ የሚከፈል መሆኑም ተብራርቷል፡፡
ዘጋቢ፡- ደርብ ሙሉየ

Related Post