የአለምን ሉላዊነት ተከትሎ ብዙ እድሎችን ይዞ የመጣዉ የገቢና የወጪ ንግድ ኢትዮጵያ ተጠቃሚ እንድትሆን የንግድ ስርአቷን እንድታዘምን ጥሪ ቀረበ፡፡
የቤስትራ ኢንተርናሽናል ድርጅት ባለቤት አቶ አብዱቃድር አብደላ በተለይ ለኒዉ ቢዝነስ ኢትዮጵያ እንደገለፁት ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚካሄደዉ የገቢና የዉጭ ንግድ ትክክለኛ የአለም አቀፍ ህግጋቶችን ባለመጠበቁ፣ የጉምሩክ አሰራርና የባንክ አሰራር ከዘመኑ ጋር አለመዘመናቸዉ ለዘርፉ ትልቅ ችግር እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
የዛሬ 17 አመት በገቢ እና ወጪ ንግድ ዘርፍ የጉምሩክ ሰራተኞችን እና በዘርፉ ለተሰማሩ ሰዎች ለማስልጠን ሙከራ አድርጌ ነበር የሚሉት አቶ አብዱ ቃድር ህብረተሰቡ ግንዛቤ ከሌላዉና የጉምሩክ ሰራተኞች ጊዜዉ የሚፈቅደዉን እዉቀትን ካልያዙ እንዲሁም መንግስት የአለም አቀፍ ንግድ ድርጅቶች ጋር አብሮ ካልሰራ ‘የትም አንደርስም በማለት ገልፀዋል፡፡
እንደ አቶ አብዱቃድር ገለፃ መንግስት ለዉጥ እንዲመጣ ከተፈለገ ህብረተሰቡ እዉቀት እንዲኖረዉ እንዲሁም የባንክና የጉምሩክ ሰራተኞችን ማተማርና አሰራሩን ዘመን በሚፈቅደዉ ደረጃ ማዘመን ይኖርበታል ብለዋል፡፡
የገቢና የወጪ ንግድ ዘርፍ ለሀገራችን ትልቅ እድል ይዞ መጥቷ ያሉት አቶ አብዱቃድር የመንግስት ዋነኛ ችግር የአሰራር እንጂ በመቶ ሺህ ለሚቆጠሩ ስራ ፈላጊዎች ስራ ልንፈጥርላቸዉ የምንችልባቸዉ ብዙ እድሎች አሉ ይላሉ እንደምሳሌነት የኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የተመረኮዘ ንግድን (e-commerce)በማንሳት፡፡
ኢትዮጵያ በንግድ ማሳለጥ ዘርፍ በእ.ኤ.አ በ2017 ከ190 የአለም ሀገራት ከነበረችበት 161 ኛ ደረጃ ሁለት እርከኖችን አሻሽላ አሁን ባለንበት የፈረንጆቹ አመት 159 ደረጃን ልትይዝ በቅታለች፡፡በቅርቡም በጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ የሚመራዉ ካቢኔ ይህን ደረጃ ለማሻሻል የንግዱን አዋጅ ማሻሻልን ጨምሮ የተለያ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ መሆኑ ይታወቃል፡፡
[embedyt] https://www.youtube.com/watch?v=umOdx-8w02o[/embedyt]