አርእስተ ዜና
Wed. Apr 24th, 2024

ባለፉት 24 ሰዓታት 1733 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

Aug29,2020
ባለፉት 24 ሰዓታት 1733 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት ለ18 ሺህ 766 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 1 ሺህ 733 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ከዚህ ባለፈም ባለፉት 24 ሰአታት የ13 ሰዎች ህይወት ማለፉን የገለፁት ሚኒስትሯ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 758 ደርሷል፡፡ በተጨማሪም ባለፉት 24 ሰአታት 586 ሰዎች ሲያገግሙ ይህን ተከትሎም ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 17 ሺህ 415 ደርሷል፡፡

አሁን ላይ 357 ሰዎች በፅኑ ህክምና ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛሉም ነው የተባለው፡፡ በኢትዮጵያ እስካሁን ለ850 ሺህ 236 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 48 ሺህ 148 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ 17 ሺህ 415ዱ ሲያገግሙ 29 ሺህ 965 ሰዎች ደግሞ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

Related Post