ህገወጥ የሰዎችን ዝውውር በተለያዩ ስልቶች መከላከል ብሎም የዝውውር ሰንሰለቱን በተቀናጀ ህግ የማስከበር ስራ መበጣጠስ በቀጣይ በትኩረት የሚሰራበት ጉዳይ መሆኑን የብሔራዊ ፍልሰት ትብብር ጥምረት አስታውቋል፡፡
ጥምረቱ በአዳማ ባደረገው ግምገማ የፍልስተኞችን መረጃ በአግባቡ መያዝ፣ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ለስራ ወደ ውጭ ከሚሄዱባቸው ሀገራት ጋር መፈራረም እና የጥምረቱን ባለድርሻ አካላት ማጠናከር የ2016 ሌላው የትኩረት ጉዳዮቹ ናቸው፡፡
በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) የሚደገፈው የብሄራዊ ፍልሰት ትብብር ጥምረት የተቋቋመው ፍልሰትን በአግባቡ ለመምራት እና ለማስተዳድር ነው፡፡
በኢጋድ የፍልሰት አስተዳደር አስተባባሪ ሙጂብ ጀማል ድርጅታቸው ጥምረቱን በመደገፍ ኢትዮጵያ በዚህ ዘርፍ የያዘችውን እቅድ እንድታሳካ የተጀመረው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
በአደማ በተካሄደው የጥምረቱ ግምገማ ከውጭ የሚመለሱ ተጎጂዎችን ለመደገፍ ፣ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ በድንበር አካባቢ ለሚኖር ፍልስት የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ እና መደበኛውን ፍልሰት በተቀመጠለት ህግ መሰረት ለመደገፍ አንዲሁም ኢመደበኛውን ፍልሰት ለመከላከል የክልልና የፌደራል ተቋማት በትኩረት ለመስራት ከስምምነት ደርሰዋል፡፡
የተንቀሳቃሽ ምስል መረጃዎች
https://youtu.be/vr0dfqIrsro