አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

የፖለቲካ ፓርቲዎች በ160 የምርጫ ክልሎች ቅሬታ አቅርበዋል

የፖለቲካ ፓርቲዎች በ160 የምርጫ ክልሎች ቅሬታ አቅርበዋል
የፖለቲካ ፓርቲዎች በ160 የምርጫ ክልሎች ቅሬታ አቅርበዋል

የፖለቲካ ፓርቲዎች በ160 የምርጫ ክልሎች ቅሬታ ማቅረባቸውን የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርትኳን ሚደቅሳ ለጋዜጠኞች መግለጫ እየሰጡ ነው፡፡ በመግለጫቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች ቅሬታ የመጨረሻ ውጤትን ሊያዘገየው ይችላል የሚል ስጋት እንዳለ የገለፁ ሲሆን ፓርቲዎቹ በ160 የምርጫ ክልሎች ቅሬታ ማቅረባቸውን ተናግረው፡፡

ቦርዱም ቅሬታዎቹ በፍጥነት መፍታት ይኖርበታል ብለዋል፡፡በማጣራት ሂደቱም የምርጫውን ውጤት ሊለውጡ የሚችሉ ቅሬታዎች ካሉ በድጋሚ ምርጫ የምናካሂድባቸው ክልሎች ሊኖሩ እንደሚችሉ በህጉ መሰረት እናውቃለን ነው ያሉት ሰብሳቢዋ፡፡

በሌላ በኩልም 942 የምርጫ ውጤት ሰነዶችን ቦርዱ እያረጋገጠ ለህዝቡ እንደሚያቀርብ ገልፀዋል፡፡ እስካሁንም 618 የሚሆኑ የምርጫ ውጤት ሰነዶች ወደ ማዕከል መጥተዋል ነው ያሉት፡፡

Related Post