አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

የመንግሥት ተቋማትን በዲጂታል የማስተሳሰር ሥራ በ120 ቀናት ተግባራዊ ይደረጋል

የመንግሥት ተቋማትን በዲጂታል የማስተሳሰር ሥራ በ120 ቀናት ተግባራዊ ይደረጋል
የመንግሥት ተቋማትን በዲጂታል የማስተሳሰር ሥራ በ120 ቀናት ተግባራዊ ይደረጋል

የመንግሥት ሥራዎችን በዲጂታል መልክ ለመሥራት የሚያስችሉ የሥራ ትሥሥር ማዕከላት በ6 ተቋማት ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ፕሮጀክቱን በጨረታ ያሸነፈው አይ-ኢ ኔትወርክ ሶሉሽን የሚሠራው ሲሆን በ120 ቀናት ውስጥ አጠናቀቆ ለማስረከብ ስምምነት አድርጓል።
የሥራ ትሥሥር ማዕከላቱ የመንግሥት ሥራዎች በግንኙነቶች ሳይቆራረጡ፣ ጊዜ እና ቦታ ሳያግዳቸው በዲጂታል መልኩ እንዲሠሩ የሚያደርግ አሠራር የሚተገበርባቸው ናቸው።

በመጀመሪያው ምዕራፍ በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ በገንዘብ ሚኒስቴር፣ በትምህርት ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን እና በብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጄክት ውስጥ ተግባራዊ የሚደረጉ ናቸው።

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ የዲጂታል 2025 ስትራቴጂ ያለግሉ ዘርፍ ተሳትፎ እውን ስለማይሆን በሁሉም የልማት ሥራዎች የግል ዘርፉ አጋር ብቻ ሳይሆን ባለቤትም እንዲሆን እየሠራን ነው ብለዋል።

በዲጂታል ፋውንዴሽን ፕሮጀከት ሥር በመተግበር ላይ ካሉት ሥራዎች ውስጥ የመንግሥት የሥራ ትሥሥር ማዕከል ልማት አንዱ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ፣ ሥርዓቱ የመንግሥት ተቋማት ሥራዎች ጊዜና ቦታ ሳይገድባቸው የሚከወኑበት መሆኑን ተናግረዋል።

በሁለተኛው ምዕራፍ ትግበራ በ50 የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና ክልሎች ጭምር ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

(ምንጭ ፟ ኢቲቪ)

Related Post