አርእስተ ዜና
Tue. Apr 16th, 2024

ባለፉት 9 ወራት የከተማ አስተዳደሩ ለ340 ሺህ በላይ ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል

Apr19,2022
ባለፉት 9 ወራት የከተማ አስተዳደሩ ለ340 ሺህ በላይ ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሯልባለፉት 9 ወራት የከተማ አስተዳደሩ ለ340 ሺህ በላይ ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል

ባለፉት 9 ወራት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ340 ሺህ 638 ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩን የከንቲባ ጽ/ቤት አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዜጎችን ሕይወት ለማሻሻል የተለያዩ ዕቅዶችን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ መሆኑን የከንቲባ ጽ/ቤት ገልጿል።
ባለፉት 9 ወራት ከሥራ ዕድል ፈጠራ ጋር የተያያዙ ሥራዎችን በተመለከተ፦ 295 ሺህ 721 ሥራ ፈላጊዎችን የመለየት እና በአንድ ማዕከል የመመዝገብ ሥራ ተሠርቷል።

በከተማዋ ለ329 ሺህ 79 ዜጎች ሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ 340 ሺህ 638 (103%) ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል። ከተፈጠረው ሥራ ዕድል ውስጥ ቋሚ 315 ሺህ 826 (92%) ጊዜያዊ 24 ሺህ 812 (8%) ሲሆን ከዩኒቨርስቲ እና ከቴክኒክ እና ሙያ ለተመረቁ ምሩቃን ለ54 ሺህ 473 (16%) የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል።

አዳዲስ ኢንተርፕራይዞችን ከማደራጀት እና ሕጋዊ ሰውነት ከመስጠት አንፃር 12 ሺህ 926 አንቀሳቃሾችን የያዙ 3 ሺህ 983 ኢንተርፕራይዞችን የማደራጀት ሥራ ተሰርቷል።

አነስተኛ መሠረተ ልማት ግንባታ በሁሉም ክፍለ ከተማ 402 የጋራ መፀዳጃ ቤት፣ 59 የጋራ መፀዳጃ ቤት ከነሻወሩ፣ 41 ሻወር በአጠቃላይ 502 ንዑስ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ግንባታቸው እየተጠናቀቀ ይገኛሉ።

የገበያ ትሥሥር አሠራርን በማዘመን ለ13 ሺህ 108 ኢንተርፕራይዞች 67 ሺህ 346 አንቀሳቃሾች የብር 5 ቢሊዮን 933 ሚሊዮን 25 ሺህ 130 የገበያ ትሥሥር መፍጠር ተችሏል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ 29 ኤግዚቢሽን እና ባዛሮችን በማዘጋጀት 2 ሺህ 785 ኢንተርፕራይዞችን በማሳተፍ የብር 53 ሚሊዮን 110 ሺህ 225 ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል ሲል የከንቲባ ጽ/ቤት በዝርዝር አሳውቋል።

(ምንጭ ፟ ኢቲቪ)

Related Post