አርእስተ ዜና
Thu. Dec 26th, 2024

የሀረሪ ክልል በአዋሽ ወንዝ ሙላት ለተጎዱ ድጋፍ አደረገ

የሀረሪ ክልል በአዋሽ ወንዝ ሙላት ለተጎዱ ድጋፍ አደረገ
የሀረሪ ክልል በአዋሽ ወንዝ ሙላት ለተጎዱ ድጋፍ አደረገ

የሀረሪ ክልል በኦሮሚያ ክልል በአዋሽ ወንዝ ሙላት ምክንያት የተጎዱ ወገኖች የሚውል የ3 ሚሊየን ብር የሚገመት ሰብዓዊ ድጋፍ አደረገ።

የክልሉ መንግስት በአዋሽ ወንዝ በመሙላት ምክንያት በኦሮሚያ ክልል ፈንታሌ ወረዳ ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች የሚውል 3 ሚሊየን ብር የሚገመት የምግብና ቀሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን የሀረሪ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ማስትና ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

የተደረገው ሰብዓዊ ድጋፍም ፓስታ፣ ማክሮኒ፣ ዱቄት፣ ዘይት እንዲሁም የተለያዩ መገልገያ ቁሳቁሶች መሆናቸውን ተመላክቷል። ድጋፋ ለማድረስም በሀገር ሽማግሌዎች፤ አባገዳዎች እና በክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የተመራ ልዑክ ወደ ስፍራው ማቅናቱን ተጠቁሟል።
(ምንጭ – የሀረሪ ክልል ኮሙኒኬሽን)

Related Post