አርእስተ ዜና
Thu. Apr 25th, 2024

የድሬደዋ ፖሊስ 20 ተሽከርካሪዎችን ተረከበ

Sep27,2020
የድሬደዋ ፖሊስ 20 ተሽከርካሪዎችን ተረከበየድሬደዋ ፖሊስ 20 ተሽከርካሪዎችን ተረከበ

የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ከአስተዳደሩ ግምታቸው 40 ሚሊየን ብር የሚጠጋ 20 ተሽከርካሪዎችን ተረከበ፡፡

ኮሚሽኑ ተሽከርካሪዎቹ በከተማዋ የህግ የበላይነትን ለማስከበር ለማደርገው እንቅስቃሴ ከፍተኛ እገዛ አላቸው ብሏል፡፡ በርክክብ ስነስረአቱ ላይ የአስተዳደሩ ከንቲባ አህመድ ቡህና ምክትል ከንቲባ ከድር ጁሀር እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ በስነስረአቱ ለይ እንደተናገሩት ኮሚሽኑ ለረጅም አመታት በተሽከርካሪ እጥረት ሲቸገር መቆየቱን አስታውሰው አስተዳደሩም ይህን ከፍተት ለመሸፈን በተለያዩ ወቅቶች ድጋፎችን ሲያደርግ ቆይቷል ብለዋል፡፡

በእለቱ ያደረግነው ድጋፍም የነበረውን ችግር ቀርፎ ኮሚሽኑ ለከተማዋ አስተማማኝ ሰላምን ለማስፈን ሚያደርገው ጥረት እገዛው የጎላ ነው ይህ ድጋፍም በቀጣይ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን በከተማዋ ላይ የሚገኘውን ማህበረሰብ ሰላምና ፀጥታ በአስተማማኝ ደረጃ ለማስከበር በሚያደርገው እንቅስቃሴ የተሽከርካሪ እጥረት ለስራው ማነቆ ሲሆን ክፍተቶቹን ለመሸፈንም በአስተዳደሩና በኮሚሽኑ ወጭ የኪራይ መኪኖችን በማቅረብና ከተቋማት በሚያገኘው ተሸከርካሪ በመታገዝ ህግ የማስከበር ተልእኮውን ሲከውን ቆይቷል፡፡

ይህም አስተዳደሩንም ሆነ ኮሚሽኑን ለከፍተኛ ወጭ መዳረጉንና የእለቱ ድጋፍም ይህን በከፍተኛ ደረጃ ሚቀርፍ መሆኑን የአስተዳደሩ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ውቢት በፍቃዱ በተሽከርካሪ ርክክቡ ወቅት ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም ባገኘነው ድጋፍ በመታገዝ ፖሊሳዊ ተልእኮዋችንን ከማህበረሰባችን ጋር በመሆን በብቃት እንወጣለንም ብለዋል፡፡ በእለቱ በድጋፍ መልክ የተበረከቱት ተሽከርካሪዎች በተናጥል ከቀረጥ ውጭ 1ሚሊየን 987ሺብር በጥቅሉም 40ሚሊየን ብር የሚጠጋ ብር ወጭ እንደሆነባቸው ከአስተዳደሩ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
(ምንጭ – የድሬደዋ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን – በዘውገ አውላቸው)

Related Post