አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

በጣልያን ኤምባሲ በቁም እስር የነበሩ የደርግ ባለስልጣናት ተለቀቁ

በጣልያን ኤምባሲ በቁም እስር የነበሩ የደርግ ባለስልጣናት ተለቀቁ
በጣልያን ኤምባሲ በቁም እስር የነበሩ የደርግ ባለስልጣናት ተለቀቁ

የቀድሞ የኢትዮጵያ ምክትል ፕሬዚዳንት ፍስሃ ደስታ በተለይ ለዶቼ ቬለ እንዳረጋገጡት -በአሁንዋ ሰዓት ጣልያን ኤምባሲ ተጠልለው የነበሩ ጓዶቻችን ኤምባሲውን ለቀው ቤታቸዉ ገብተዋል፤ ለእነሱ በጎ የተመኛችሁ ሁሉ እነኳን ደስ ያላቹህ።» ብለዋል።

በጣሊያን ኤምባሲ በቁም እስር ላይ የነበሩት የሞት ፍርደኞቹ ሁለት የደርግ ዘመነ መንግሥት ባለሥልጣናት የቀድሞ ወታደራዊ መኮንኖች የ85 ዓመቱ ሌተናል ኮሎኔል ብርሃኑ ባይህ እና የ77 ዓመቱ ሌተናል ጀነራል አዲስ ተድላ በአመክሮ እንዲፈቱ የፌደራሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መጠየቁ ይታወቃል።

ባለሥልጣናቱ በዘር ማጥፋት ወንጀል የተከሰሱ መሆኑን ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ በአመክሮ እንዲፈቱ ቀድሞ ውሳኔውን ላሳለፈው ፍርድ ቤት ጥያቄ አቅርቦ ይሁንታን ካገኘ በኋላ ነዉ የቁም እስረኞቹ በነፃ ለመዉጣት የበቁት፡፡ ከዚህ ቀደም ሲል ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የፍርደኞቹ ውሳኔ ከሞት ወደ እድሜ ልክ እንዲቀየር አፅድቀዉ ነበር፡፡

ይህን ተከትሎም ዐቃቤ ሕግ ሁለቱ ግለሰቦች ላለፉት 30 ዓመታት በአዲስ አበባ ቤላ የሚገኘው ጣልያን ኤምባሲ በቁም እስር ላይ የቆዩ መሆናቸውን መነሻ በማድግ በአመክሮ ቢፈቱ ሲል ምክረ ሃሳቡን ለፍርድ ቤት ካቀረበ በኋላ ዛሬ መፈታታቸዉ ተሰምቶአል።

በኤምባሲው ተጠልለው የነበሩት የቀድሞ ወታደራዊ መኮንኖች የ85 ዓመቱ ሌተናል ኮሎኔል ብርሃኑ ባይህ እና የ77 ዓመቱ ሌተናል ጀነራል አዲስ ተድላ ናቸዉ።

(ምንጭ -Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

Related Post