አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች በኢትዮጵያ ለገበያ ቀረቡ

በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች በኢትዮጵያ ለገበያ ቀረቡ
በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች በኢትዮጵያ ለገበያ ቀረቡ

ግሪንቴክ ኢትዮጵያ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በኢትዮጵያ ለገበያ አቀረበ።

ግሪንቴክ ኢትዮጵያ ለሀገር ውስጥ ገበያ ያቀረባቸውን በፀሐይና በኤሌክትሪክ ታዳሽ ኃይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል። መግለጫውን የሰጡት የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍጹም ደሬሳ “ግሪንቴክ ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል የቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመንቀሳቀስ በተለይም በፀሐይና ኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰሩ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት እየሰራ ነው” ብለዋል።



በዚህም ከአካባቢ ብክለት የጸዱና የአረንጓዴ ኃይል ልማት አካል የሆኑ በፀሐይና ኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ድርጅቱ ለገበያ አቅርቧል ነው ያሉት።
ተሽከርካሪዎቹ በአረንጓዴ የሃይል ዘርፍ በአለም አቀፍና በሀገር ውስጥ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን ያማከሉ መሆናቸውን አብራርተው የተሽከርካሪዎቹ አይነት አምስት ሰው ከሚጭኑ አነስተኛ የቤት መኪናዎች ጀምሮ ሚኒባሶችና ረጅም ርቀት የሚጓዙ አውቶቡሶች የተካተተበት ነው ብለዋል።

የድርጅቱ የኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ ቴዎድሮስ ታደሰ በበኩላቸው ተሽከርካሪዎቹ በሙሉ ጊዜ ቻርጅ 320 ኪሎ ሜትር ርቅት ድረስ እንደሚጓዙ ተናግረው፤ ከግሪን ትራንስፖርት ጋር በመሆን በ40 እና 60 የባለቤትነት ድርሻ ለአሽከርካሪዎች እንደሚተላለፉ ገልጸዋል።

“የታዳሽ ኃይልን በመጠቀማቸው በከፍተኛ ደረጃ የመለዋወጫና የጥገና ወጪን የሚቀንሱ ተሽከርካሪዎቹ ናቸው” ሲሉ አስረድተው፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለነዳጅና ለመለዋወጫ የሚውለውን የውጭ ምንዛሬ በአንድ ሦስተኛ በመቀነስ አስተዋጽኦ ያደርጋል ብለዋል። ግሪንቴክ ኢትዮጵያ በቅርቡ አምስት ሺህ ገደማ በፀሐይና ኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ለገበያ እንደሚያቀርብም በመግለጫው ተመልክቷል።


Related Post