አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

በአማራ እና አፋር የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ 1.6 ቢሊየን ብር ጉዳት ደረሰ

በአማራ እና አፋር የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ 1.6 ቢሊየን ብር ጉዳት ደረሰ
በአማራ እና አፋር የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ 1.6 ቢሊየን ብር ጉዳት ደረሰ

በአማራ እና አፋር ክልሎች አሸባሪዉ ሕወሓት በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ የአንድ ነጥብ ቢሊዮን ብር ጉዳት ማድረሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ገለጸ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ የደረሰዉን ጉዳት እና የጥገና ስራዎችን በሚመለከት ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

አሸባሪዉ ሕዉሓት የቻለዉን ዘርፎ ያልቻለዉን አዉድሞ መሄዱን የገለጹት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ፤ ተቋሙ ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ በአብዛኛዉ የአማራና አፋር ክልሎች ጥገና በማድረግ ዜጎች አገልግልቱን በፍጥነት እንዲያገኙ አድርጓል ብለዋል። አሁንም የተወሰኑ የትገራይ አዋሳኝ የሆኑ የአማራ እና የአፋር አከባቢዎች የኤሌክትሪክ ሀይል እንዳላገኙም አቶ ሞገስ አስታውቀዋል።

ምንጭ – (ኢ ፕ ድ)

Related Post