አርእስተ ዜና
Thu. Dec 26th, 2024

በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ዙርያ ውይይት ተካሄደ

በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ዙርያ ውይይት ተካሄደ
በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ዙርያ ውይይት ተካሄደ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በተቋሙ የ10 ዓመት መሪ ዕቅድ፣ የበጀት ዓመቱ እቅድ እና ከሙስናና ከሕዝብ ሃብት ምዝበራ ወንጀሎች ጋር በተያያዙ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ እና ፍትህ ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የዲሞክራሲና ሰብአዊ መብት ተቋማት ኃላፊዎች፣ የመንግስትና የግል መገናኛ ብዙሃን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ የመድረኩን አላማ አስመልክተው እንደተናገሩት የሕግ አወጣጥና አተገባበር፣ ሰብአዊ መብት አያያዘ እና የህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ጉዳዮች በተቋሙ የ10 ዓመቱ መሪ ዕቅድና የበጀት ዓመቱ ዕቅድ የተካተቱ ተግባራት መሆናቸውን ጠቁመው ስራዎችን በቅልጥፍናና በቅንጅት ለመስራትና ውጤታማ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ሚና የጎላ በመሆኑ በትብብር አብሮ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

የሕግ ጉዳዮች ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የህግ አማካሪ የሆኑት አቶ አሰግድ አያሌው ባቀረቡት የጥናት ሰነድም ከላይ በርዕሱ ላይ የተጠቀሱትን የወንጀል አይነቶች ከመከላከል እና ከመዋጋት አንጻር ስትራቴጂክ ዕቅዱ ያካተታቸውን ነጥቦች እና ራዕዮች እውን ለማድረግ 3 የትኩረት መስኮችን፣ 4 እይታዎችን እና 16 ስትራቴጂያዊ ግቦችን መሰረት በማድረግ የተዋቀረ መሆኑን አውስተዋል፡፡

በተያያዘ ዜናም ከሙስና እና ከህዝብ ሀብት ምዝበራ ጋር በተያያዘ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ምክትል ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ዘላለም ፍቃዱ የ2012 በጀት አመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2013 በጀት ዓመት ዕቅድ ያቀረቡ ሲሆን በበጀት አመቱ ዕቅድም የህዝብና የመንግስት ጥቅም ያላቸውን ትላልቅ የሙስና ወንጀል ጉዳዮችን ከምርመራ ጀምሮ ልዩ ትኩረት በመስጠት እንደሚሰራና ለዚህም ዕቅድ ስኬት የባለድርሻ አካላት ሚና የላቀ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

በመጨርሻም የውይይቱ ተሳታፊዎች የጋራ መድረኩ መዘጋጀቱን አመስግነው በቀረበው የውይይት መነሻ ሰነድ ላይ የተለያዩ ግብአቶችን እና አስተያየቶችን ሰጥተዋል፤ የተለያዩ ጥያቄዎችንም አንስተዋል፡፡ ለተነሱ ጥያቄዎችም ም/ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ፍቃዱ ፀጋ፣ የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጽ/ቤት ኃላፊው አቶ ጥላሁን ወርቁ እና የተቋሙ የስራ ክፍል ኃላፊዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
(ምንጭ – የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ)

Related Post