አርእስተ ዜና
Sun. Apr 28th, 2024

የአገር ክህደት ወንጀል በፈጸሙ የመያዣ ትዕዛዝ መውጣቱ ተገለፀ

Nov19,2020
የአገር ክህደት ወንጀል በፈጸሙ የመያዣ ትዕዛዝ መውጣቱ ተገለፀየአገር ክህደት ወንጀል በፈጸሙ የመያዣ ትዕዛዝ መውጣቱ ተገለፀ

የአገር ክህደት ወንጀል በፈጸሙ 76 ጀነራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የበታች ሹማምንቶች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ መውጣቱ ተገለፀ፡፡

በትግራይ ክልል በሚገኘው በሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈፀም አገር የማፍረስ ሴራ አቅደው ሲንቀሳቀሱ የነበሩና የአገር ክህደት ወንጀል የፈጸሙ የጁንታው ህዋሃት ወንበዴ ቡድን የበላይ አመራሮችን አድኖ ለህግ ለማቅረብ ከሳምንት በፊት ማለትም ህዳር 3/2013ዓ.ም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንደወጣባቸው መገለፁ ይታወቃል፡፡

በተመሳሳይም ከጁንታው የህዋሃት ቡድን አባላት ጋር እየተገናኙ አገር በማፍረስ ሴራ ውስጥ በመሳተፍ የሀገር ክህደት ወንጀል በፈፀሙ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጀነራል መኮንኖች፣ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የበታች ሹማምንቶች እንዲሁም በፖሊስ አመራሮች ላይ የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ እንደወጣባቸው ያስታወሰው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን መግለጫ፤ከጁንታው የህዋሃት የጥፋት ቡድን አገር የማተራመስና የማፍረስ ሴራ እጃቸውን ባስገቡና በአገር ክህደት ወንጀል የተሳተፉ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን ተከታትሎ በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ የማድረግ ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ኮሚሽኑ ገልጿል።

የአገር ክህደት ወንጀል በፈጸሙ የመያዣ ትዕዛዝ መውጣቱ ተገለፀ
የአገር ክህደት ወንጀል በፈጸሙ የመያዣ ትዕዛዝ መውጣቱ ተገለፀ
በዚህም መሰረት በሀገር መከላከያ ሠራዊት በስራ ላይ ያሉና በጡረታ የተሰናበቱ ጀነራል መኮንኖች፣ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የበታች ሹማምንቶች የተጣለባቸውን ህዝባዊና አገራዊ አደራና ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው እና የጁንታው የህወሃት ቡድን የሴራ አካል በመሆን የአገር ክህደት ወንጀል የፈጸሙ ተጠርጣሪዎችንም አድኖ ለህግ ለማቅረብ የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ እንደወጠባቸው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን መግለፅ ይወዳል፡፡

የሀገር ህልውናን አደጋ ላይ በመጣልና ህገ-መንግስቱንና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል በመናድ ወንጀል ውስጥ በመሳተፍ የሚፈለጉትና የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸው በስራ ላይ ያሉና በጡረታ የተሰናበቱ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጀነራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የበታች ሹማምንቶች ፡-

የአገር ክህደት ወንጀል በፈጸሙ የመያዣ ትዕዛዝ መውጣቱ ተገለፀ
የአገር ክህደት ወንጀል በፈጸሙ የመያዣ ትዕዛዝ መውጣቱ ተገለፀ

1. ሜጀር ጀነራል ማህሾ በየነ
2. ሜጀር ጀነራል ሀለፎም እጂጉ
3. ብርጋዴል ጀነራል ፍትዊ ፀሃዬ ገ/እግዚአብሔር
4. ብርጋዴል ጀነራል ግደይ ሀይሉ ገ/እግዚአብሔር
5. ብርጋዴል ጀነራል ወልደ ጊዮርጊስ
6. ብርጋዴል ጀነራል ጉሽ ገብሬ
7. ብርጋዴል ጀነራል ከበደ ፍቃዱ
8. ብርጋዴል ጀነራል ገብረጊዮርጊስ
9. ብርጋዴል ጀነራል ህንፃ ወ/ገወርጊስ
10. ኮሎኔል ተወልደ ገ/ትንሳይ
11. ኮሎኔል ንጉሴ ገብሩ
12. ኮሎኔል መብራቱ አሰፋ /አልማዝ/
13. ኮሎኔል ዘገየ ንጉስ
14. ኮሎኔል ያለም
15. ኮሎኔል መብራቱ ተድላ
16. ኮሎኔል ነጋሽ መብራቱ
17. ኮሎኔል ተክሉ በላይ
18. ኮሎኔል ጥጋቡ መለስ
19. ኮሎኔል ግርማ ተካ
20. ኮሎኔል ሙሉጌታ ገብረክርስቶስ ነጋሽ
21. ኮሎኔል አራሞ ገ/መድህን
22. ኮሎኔል ተስፋዬ ገ/መድህን
23. ኮሎኔል ግርማል አለማየሁ
24. ኮሎኔል ነጋሽ አለፎም
25. ኮሎኔል ተስፋዬ ምሩፅ
26. ኮሎኔል ካሳየ አሰፋ
27. ኮሎኔል ነጋሲ ታደሰ ስዩም
28. ኮሎኔል ኪሮስ ሓጎስ ገ/ዝጋብሔር
29. ኮሎኔል ሙርፅ ገብረሊባኖስ አብርሃ
30. ኮሎኔል ሓ/ስላሴ ኪሮስ ተስፋይ
31. ኮሎኔል ምሩፅ በርሔ/ተወርወር/
32. ኮሎኔል ሀይለስላሴ አሰፋ
33. ኮሎኔል ደርበው ኃጎስ
34. ኮሎኔል ወልዴ ሀጎስ
35. ኮሎኔል ንጉሴ አማረ
36. ኮሎኔል ነጋሲ ታደሰ
37. ኮሎኔል ባራኪ /ወዲ ራያ/
38. ኮሎኔል ከበደ ገ/ሚካኤል
39. ኮሎኔል ፀጋ ብርሀን ገ/እዜር
40. ኮሎኔል ዘሩ ሀ/መለኮት
41. ኮሎኔል ሀይለ መዝገብ
42. ኮሎኔል አርአያ ገብሩ ግደይ
43. ኮሎኔል የማነ ገ/ሚካኤል
44. ኮሎኔል ዘሩ መረሳ
45. ኮሎኔል ልጃለም ገ/ህይወት
46. ኮሎኔል ፍሰሀ ግደይ
47. ኮሎኔል ገብረመስቀል ወልደገብርኤል
48. ኮሎኔል ወልዱሀጎስ ገብሩ
49. ኮሎኔል ገ/ሚካኤል ሀጎስ
50. ኮሎኔል ስብሀቱ መብራቱ
51. ኮሎኔል ጣሰው ወ/ጊዮርጊስ
52. ኮሎኔል ገ/እግዚያብሔር አለምሰገድ
53. ኮሎኔል ነጋሲ ታደሰ
54. ኮሎኔል ተክለ በላይ
55. ሌተናል ኮሎኔል ተወልደ አብርሃ ወ/ሚካኤል
56. ሌተናል ኮሎኔል ሙዘይ ተሰማ ስዩም
57. ሌተናል ኮሎኔል ፍስሃ በየነ ገ/ኪዳን
58. ሌተናል ኮሎኔል ምሩፅ ወ/አረጋይ ገ/መስቀል
59. ሌተናል ኮሎኔል ሙሩፅ በርሀ ኣበራ
60. ሌተናል ኮሎኔል ፀሀዬ ሀጎስ
61. ሌተናል ኮሎኔል ሀጎስ ኪሮስ
62. ሌተናል ኮሎኔል ገብረ ህንፃ ሀዲሽ
63. ሌተናል ኮሎኔል ፈለቀ አይጠገብ
64. ሻለቃ አስገዶም መስፍን
65. ሻምበል ባሻ ሙእዝ መልካም
66. ሻምበል አርአያ ተ/ኃይማኖት
67. ሻምበል ተስፋ ህይወት ………ናቸው ።

ከላይ ስማቸው የተዘረዘረው ጀነራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የበታች ሹማምንቶች ከሀገር መከላከያ ሰራዊት እሴቶች መካከል ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም የሚለውን ወደ ጎን በመተው የወንበዴው ጁንታ ህዋሃት የጥፋት ቡድን የሴራ አካል በመሆን በወንጀል የሚፈለጉ መሆናቸውን ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በመግለጫው አሳውቋል፡፡

የአገር ክህደት ወንጀል በፈጸሙ የመያዣ ትዕዛዝ መውጣቱ ተገለፀ
የአገር ክህደት ወንጀል በፈጸሙ የመያዣ ትዕዛዝ መውጣቱ ተገለፀ
በመሆኑም መላው የሃገራችን ህዝቦች በተለይም ደግሞ የትግራይ ህዝብ፤የክልሉ ልዩ ሀይል አባላትና ሚሊሻዎች እንዲሁም የሀገር መከላከያ ሰራዊት፤የአገራችን የፖሊስ ሰራዊትና የደህንነት ተቋማት እነዚህን የጁንታውን የህዋሃት የጥፋት ቡድን ተፈላጊዎች አድኖ ለህግ ለማቅረብ እየተደረገ ባለው ጥረት በያላችሁበት የድርሻችሁን እንድትወጡ ኮሚሽኑ ጥሪ እያቀረብ፤ በቀጣይም በጁንታው የህዋሃት የጥፋት ቡድን አገር የማተራመስና የማፍረስ ሴራ እንዲሁም በአገር ክህደት ወንጀል የተሳተፉትንና በየትኛውም የኃላፊነት ደረጃና መዋቅር ላይ ያሉ ተጠርጣሪዎችን ተከታትሎ በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ የማድረግ ስራውም ሆነ በጉዳዩ ዙሪያ ተከታታይ መረጃዎችን በመገናኛ ብዙሃን በኩል ለህብረተሰቡ ይፋ የማድረግ ሂደቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

Related Post