አርእስተ ዜና
Thu. Dec 26th, 2024

የምርምር ተቋሙ የፈረንሳይ ዶሮዎችን ለኢትዮጵያ አርሶ አደሮች አስተዋወቀ

የምርምር ተቋሙ የፈረንሳይ ዶሮዎችን ለኢትዮጵያ አርሶ አደሮች አስተዋወቀ
የምርምር ተቋሙ የፈረንሳይ ዶሮዎችን ለኢትዮጵያ አርሶ አደሮች አስተዋወቀ

በኢትዮጵያና ኬኒያ ሀገር የሚሰራዉ የአለም አቀፍ የእንስሳት ምርምር ተቋም (International Livestock Research Institute) የፈረንሳይ የዶሮ ዝርያዎችን አላምዶ ለኢትዮጵያዊያን አርሶአደሮች እያቀረበ መሆኑን ተገለፀ፡፡

የተቋሙ መሪ ተመራማሪ ዶ/ር ታደለ ደሴ ለኒዉ ቢዝነስ ኢትዮጵያ አንደገለፁት ምርታማነታቸዉ ጥሩ የሆኑና ለሀገራችን የአየር ንብረት ተስማሚ የሆኑ የዶሮ ዝርያዎችን ከተለያዩ የአለም ሀገራት በማምጣት እንዳላመዱ ገለፀዋል፡፡በግል ኩባንያዎች አማካኝነት የተመረጠዉ ሳሱን የተባለዉ የፈረንሳይ የዶሮ ዝርያ ለአርሶ አደሮች እንደደረሰም ተናግረዋል፡፡

በጥናትና ምርምር በመጠቀም ምርታማነትን ማሳደግ የመንግስት ኃላፊነት አድርጎ መውሰድ በሀገራችን የተለመደ ሲሆን ተቋሙ ግን ለአርሶ አደሩ ተስማሚ የሆኑ ዶሮዎችን በማስተዋወቅ ከግል ኩባንያዎች ጋር በመስራት ለገበሬዎች ማቀረቡን ዶ/ር ታደሰ ደሴ ተናግረዋል፡፡ድርጅቱ ኢትዮ ቺኪንና ሀዋሳ የዶሮ እርባታ የተባሉ በሁለት የግል ኩባንያዎች አማካኝነት አዲሶቹን የፈረንሳይ ዝርያዎችን ለአርሶ አደሮች እያቀረቡ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ከፈረንሳይ የመጡት ዶሮዎች በኢትዮጵያ ዉስጥ ከሚገኙ ዶሮዎች ሲነፃፀሩ እድገታቸዉ ሶስት እጥፍ ሲሆን በእንቁላል ረገድም ከእጥፍ በላይ የእንቁላል ምርት እንደሚሰጡ ተገልጿል፡፡ስለ ዶሮዎች ማላመድም ሂደት ላነሳንላቸዉ ጥያቄ ዶ/ር ታደለ የሚከተለዉን ማብራሪያ ሰጥተዉናል፡፡

ዘርፉ ብዙ ኢንቨስትመንት ካለመፈለጉ አኳያ ለብዙ ወጣቶች የስራ እድል እየፈጠረ ነዉ ብለዋል፡፡ጥናቱ በተደረገበት አመትም ከፕሮቲን እጥረት የሚመጣዉን የመቀንጨር ችግር ከመቀነስ አንፃር ያካሄዱት ጥናት ዉጤት አመርቂ መሆኑን ዶ/ር ታደለ ደሴ ገልፀዋል፡፡

የአለም አቀፍ የእንስሳት ምርምር ተቋም በኢትዮጵያ ምርታማ ዶሮዎችን የማላመድ ስራ ለአርሶ አደሮች የሚሰራ ሲሆን ይህ ፕሮግራም በአፍሪካ ደረጃ እያካሄደ ያለዉ የፕግራሙ አንዱ አካል ነዉ፡፡ተቋሙም በአለም አቀፍ ደረጃ ከ 15 ተመሳሳይ ድርጅቶች ጋር አብሮ ይሰራል፡፡
[embedyt] https://www.youtube.com/watch?v=qUS-EKVEA8k[/embedyt]

Related Post