አርእስተ ዜና
Fri. Nov 22nd, 2024

የንግድ ስራ ገቢ ግብር

የንግድ ስራ ገቢ ግብር
የንግድ ስራ ገቢ ግብር

የንግድ ስራ ገቢ የሚባለው፡-

1. ግብር ከፋዩ ዕቃዎችን በማስተላለፍ እና አገልግሎቶችን በመስጠት የሚያገኘውን የገንዘብ መጠን ጨምሮ በግብር ዓመቱ ከንግድ ስራ ያገኘው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን፣
2. የንግድ ስራ ሃብትን በማስተላለፍ የሚገኝ የገንዘብ መጠን (ከመዝገብ ዋጋ በላይ ያለው ዋጋ)፣
3. በአዋጅ መሠረት የግብር ከፋዩ ገቢ ተደርገው የተወሰዱ ሌሎች ማናቸውም ገቢዎች፣

4. የካፒታል ንብረት የሆነን የንግድ ስራ ሃብት በማስተላለፍ በሚገኘው ጥቅም ላይ ሁለት ግብሮች ሊወሰኑ ይችላሉ፡፡
— የንግድ ትርፍ ግብር
— የካፒታል ዋጋ ዕድገት ግብር

5. ለንግድ ስራው ሃብት የተደረገው ወጪ ከንግድ ስራው ሀብት የተጣራ የመዝገብ ዋጋ የሚበልጠው የገንዘብ መጠን በንግድ ስራ ገቢ ውስጥ የሚካተት ሲሆን ከወጪው በላይ የሚገኘው ጥቅም ደግሞ የካፒታል ዋጋ ዕድገት ግብር ይከፈልበታል፡፡

ምንጭ – የገቢዎች ሚኒስቴር

Related Post