አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

ቴክኖ ሞባይል ሁለት አዲስ የሞባይል ስልኮችን ይፋ አደረገ

ቴክኖ ሞባይል ሁለት አዲስ የሞባይል ስልኮችን ይፋ አደረገ
ቴክኖ ሞባይል ሁለት አዲስ የሞባይል ስልኮችን ይፋ አደረገ

የሞባይል ቴክኖሎጂ ብራንዶች አምራች የሆነው እና ከ70 በላይ ሀገራት ምርቶቹን በስፋት የሚያቀርበው ቴክኖ ሞባይል አዲሱ ምርት የሆነውን ስፓርክ 20 ፕሮ ፕላስ (Spark 20 Pro+) የተሰኘ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተራቀቀ፣ እጅግ ከፍተኛ የካሜራ ጥራትና የፕሮሰሰር አቅም፣ ለረጅም ጊዜ መቆየት የሚችል ባትሪ፣ ማራኪ ቅርጽ እና ውበት ያለው የመጨረሻው የቴክኖሎጂ ውጤት የያዘውን እንዲሁም ደንበኞች የላቀ የአገልግሎት ተሞክሮ እንዲኖራቸው የሚያስችለውን የስማርት ሞባይል ስልክ ሞዴል በአዲስ አበባ ፍሬንድሽፕ ፓርክ ልዩ እና ደማቅ በሆነ ዝግጅት አስተዋወቀ።

ቴክኖ ሞባይል አዲሱን ስፓርክ ፕሮ ፕላስ ሞዴል በዛሬው እለት በይፋ ያስተዋወቀበትን ልዩ ዝግጅት የመንግስት ባለስልጣናት፣ የቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ ከፍተኛ አመራሮች፣ የኢትዮጲያ አንጋፋ የእግር ተጫዋቾች እና አመራሮች እንዲሁም የስፖርቱ ቤተሰብ የታደሙ ሲሆን በኢትዮጲያ የስፖርቱ ዘርፍ እድገት እና የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ተሳትሮ እውን እንዲሆን ከፍተኛ ሚና የነበራቸውን የቀድሞ የኢትዮጲያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋጮች፣ አሰልጣኞች እና የስፖርት ጋዜጠኞችን የማመስገኛ መርሃግበር ያካተተም ነበር።

በስፖርቱ አለም ተውዳጅ ከሚባሉት ዝግጅቶች አንዱ የሆነውን የአፍሪካ ዋንጫ የእግር ኳስ ውድድር ይፋዊ ስፖንሰር የሆነው ቴክኖ ሞባይል ይህን አዲሱን የሞባይል ሞዴል ከዚሁ የአህጉራዊ ስፖርት መረሀግብር ጋር በማስተሳሰር ቴክኖሎጂ እና ስፖርቱ ያጣመረ የማስተዋወቅ ልዩ ልዩ እንቅስቃሴዎችን በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት እያከናወነ ይገኛል። ቴክኖሎጂን ያለ ልዩነት ለሁሉም በጥራት ለማዳረስ እየሰራ የሚገኘው ቴክኖ ሞባይል የአዲሱን ትውልድ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ፍሎጎት ለሟሟላት እና ዘመኑ የደረሰበትን የተራቀቀ የምርት ዘዴዎችን በመጠቀም በሚያመርታቸው ተወዳጅ የሞባይል ሞዴሎች ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የቴክኖሎጂ ሽፋን ተደራሽ ለማድረግ የተያዘውን አላማ በመደገፍ መጠነ ሰፊ ስራዎችን ሲተገብር እንደቆየ የሚታወቅ ነው።

ላለፉት አመታት በአዳዲስ እና ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በመታገዝ ለአለም ገበያ የሚያቀርባቸው የሞባይል ሞዴሎች አንዱ የሆነው እና የተጠቃሚዎች ፍላጎት በማሟላት በደንበኞቹ ዘንድ ተወዳጅነትን ያፈራው ስፓርክ ሲሪየስ ሞዴል በእጅጉ ተሻሽሎ ከቴክኖ ሞባይል ቀርባል። አዲሱ ስፓርክ 20 ፕሮ ፕላስ ሞዴል በ108 ሜጋ ፒክስል አልትራ ሴንሴቲቭ (ultra-sensitive) የካሜራ ጥራት የተገጠመለት ሲሆን በ ኤ.አይ (AI) ሲስተም በመታገዝ በየትኛውም አይነት የብርሀን መጠን በምሽት ሆነ በቀን ጥርት ያሉ ፎቶዎችን ማንሳት ያስችላል። በከፍተኛ ፍጥነት የተለያዩ መተግበሪያዎችን ያለእንክን እንዲያስተናግድ የሚያስችለው (G99 ultra boost) የተሰኘ ፕሮሰሰር ያለው መሆኑ እና 6.78 ኢንች አሞሌድ ስክሪን በ120Hz ሪፍሬሽ ሬት የሆነው ስፓርክ 20 ፕሮ ፕላስ ሲጠቀሙበት ያለምንም እንከን በቅልጥፍና አንዲያገለግል ያደርገዋል፣ የሞዴሉንም የመያዝ አቅሙን በመጨመር 256 ጂቢ ሚሞሪ በ16 ጂቢ ራም ጋር የቀረበ ሲሆን 5000 mAh አቅም ያለው ባትሪ ከ33W ሱፐር ቻርጅንግ ሲስተም ያለው ሲሆን በአጭር ጊዜ 100% ባትሪ ቻርጅ ማድረግ አቅም ያለው የስልክ ሞዴል ነው።

በዚህ በምረቃ ወቅት ንግግር የደረጉት የቴክኖ ሞባይል ኢትዮጲያ ብራንድ ማኔጀር አቶ ኤሊክ ኋንግ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደጠቀሱት ‘’ይህ በላቀ ቴክኖሎጂ በልዩ መልክ የተመረተውን አዲሱ (spark 20 pro+) በዚህ አህጉራዊ ውድድር ወቅት በማስተዋወቃችን ኩራት ይሰማናል። በኢትዮጲያ ብሎም በአፍሪካ እየጨመረ የመጣውን የቴክኖሎጂ ፍላጎት አለም ከደረሰመት የስማርት ስልክ ቴክኖሎጂ ጋር በማጣመር የአህጉሪቷን እድገት ለማፋጠን ለሚደረገው ርብርብ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ እንደሚሆን አንጠራጠርም። ከዚም በተጨማሪ ድርጅታችን ቴክኖ ሞባይል ተወዳጅ የሆነውን አዲሱን ስፓርክ (spark 20 pro+) ስልክ ከማስተዋወቅ ባለፈ የብዙ እግር ኳስ ከዋክብት መፍለቅያ በሆነችው አፍሪካ የ2024ቱን የአፍሪካ የእግር ኳስ ዋንጫ ይፋዊ ስፖንሰር በመሆኑ ደስታችን ላቅ ያለነው።’’

ቴክኖ ሞባይል ዘመኑ የደረሰበት የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለአለም ገበያ በማቅረም ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘ ሲሆን ከሚያመርታቸው ስልኮች በተጨማሪ በፈጠራ እና በአገልግሎት ብቃት የዳበሩ ስማርት ሰዐት፣ ላፕቶፕ እና ሃይኦኤስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም (HiOS operating system) የሚያመርት ሲሆን የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በስፋት ተደራሽ ለማድረግ እና በአዳዲስ ፈጠራዎች ግንባር ቀደም ለመሆን የሚሰራ አለም አቀፍ ብራንድ ነው።

Related Post