አርእስተ ዜና
Fri. Nov 22nd, 2024

የበጎ አድራጎት ድርጅት በታክስ ተመላሽ ስርዓት ስለሚስተናገድበት ሁኔታ

የበጎ አድራጎት ድርጅት በታክስ ተመላሽ ስርዓት ስለሚስተናገድበት ሁኔታ
የበጎ አድራጎት ድርጅት በታክስ ተመላሽ ስርዓት ስለሚስተናገድበት ሁኔታ

ለሰብአዊ እርዳታ ስለሚውሉ እቃዎችና አገልግሎቶች የታክስ ነፃ መብት አፈፃፀምን አስመልክቶ በወጣ መመሪያ ቁጥር 23/2001 መሰረት የበጎ አድራጎት ድርጅት በታክስ ተመላሽ ስርዓት ስለሚስተናገድበት ሁኔታ የሚከተለውን ይላል።

የበጎ አድራጎት ድርጅት ለሰብአዊ እርዳታ ወደ አገር የሚያስገባቸውና በአገር ውስጥ የሚገዛቸው እቃዎች በታክስ ተመላሽ ሥርዓት የሚስተናገዱት ድርጅቱ፡-
1. የውጭ አገር ከሆነ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከገንዘብ ሚኒስቴር እውቅና ማግኘቱን የሚያሳይ ማስረጃ ሲያቀርብ፣
2. አገር በቀል ከሆነ በፍትህ ሚኒስቴር ወይም በሚመለከታቸው የክልል መስተዳደር አካል የተመዘገበ፣ የዘመኑ የታደሰ የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ለእርዳታ የተሰማራ መሆኑ ከግብርና ሚኒስቴር የተሰጠ ማረጋገጫ ሲያቀርብ፣

3. ድርጅቱ የእርዳታ ፕሮገራሙን ለግብርና ሚኒስቴር እና አግባብነት ላላቸው ተቋሞች አቅርቦ ከታክስ ነፃ ወይም በዜሮ ምጣኔ የሚስተናገደውን አቅርቦት ዝርዝርና መጠን፣ እንዲሁም የቆይታ ጊዜን የያዘ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተሰጠ ማስረጃ ያቀረበ ሲሆን ብቻ ነው፡፡
ምንጭ – የገቢዎች ሚኒስቴር

የተንቀሳቃሽ ምስል ዜናዎች
https://youtu.be/xDvZI2yd_Vk

Related Post