አርእስተ ዜና
Sat. Nov 23rd, 2024

የስደተኞች ተፅዕኖ ምላሽ የልማት ፕሮጀክት ተበሰረ

የስደተኞች ተፅዕኖ ምላሽ የልማት ፕሮጀክት ተበሰረ
የስደተኞች ተፅዕኖ ምላሽ የልማት ፕሮጀክት ተበሰረ

በግብርና ሚኒስቴር የሁለተኛ ምዕራፍ የስደተኞች ተፅዕኖ ምላሽ የልማት ፕሮጀክትን ወደ ሥራ ለማስገባት የፌዴራልና የክልሎች ከፍተኛ አመረራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም የባለድርሻ ተቋማት ኃላፊዎች በተገኙበት የማብሰሪያ መርሀ ግብር ተካሄዷል፡፡

የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር መለስ መኮንን መረሀ ግብሩን በንግግር ሲከፍቱ እንደገለፁት 1ኛ ምዕራፍ የስደተኞች ተፅዕኖ ምላሽ የልማት ፕሮጀክት ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ ስደተኞች የተጠለሉባቸው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ፣ በሱማሌ፣ በአፋርና በትግራይ ክልሎች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ተፅዕኖን ለመቀነስ በርካታ የልማት ተግባራት አከናውኗል፡፡

ፕሮጀክቱ የአካባቢውን ማህበረሰብ በማሳተፍ 225 የ1ኛ ደረጃ ት/ቤቶች፣ 98 የሰው ጤና ኬላዎች፣ 48 የእንስሳት ጤና ኬላዎች፣ 520 ኪ.ሜ የገጠር መንገድ፣ ….. በመገንባት ውጤታማ ስራ በመስራቱ ከ1.3 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችለዋል ብለዋል፡፡ በዘላቂ የአካባቢ አያየዝና የቤተሰብ ኑሮ ማሻሻል በኩልም አመርቂ ሥራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል፡፡

የምዕራፍ አንድ ትግበራ መልካም አፈፃፀም መሰረት በማድረግም የምዕራፍ ሁለት የስደተኞች ተፅዕኖ ምላሽ የልማት ፕሮጀክት እንዲቀጥል በመንግስት መወሰኑንና የአማራ ክልልን ጨምሮ በ6 ክልሎች እንደሚተገበር ጠቅሰው ለተግባራዊነቱ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በኃላፊነት የድርሻቸውን እንዲወጡ ሚኒስትር ዴኤታው አሳስበዋል፡፡

በዓለም ባንክ የቀጠናው የ1ኛና የ2ኛ ምዕራፍ የስደተኞች ተፅዕኖ ምላሽ የልማት ፕሮጀክት ትግበራ ቡድን መሪ ሚስተር ማትው ስቲፈን በበኩላቸው አለም ባንክ 100 ሚሊዮን ዶላር በመበጀት ስደተኞች ባሉበት አካባቢዎች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ተፅዕኖን ለመቀነስ በ1ኛው ምዕራፍ ፕሮጀክቱ የተከናወኑ ውጤታማ ሥራዎች በኢትዮጵያ መንግስት መልካም ትብብር መሆኑን ተናግረው 180 ሚሊዮን ዶላር የተመደበለት የ2ኛ ምዕራፍ የስደተኞች ተፅዕኖ ምላሽ የልማት ፕሮጀክትም ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ቅንጅታዊ አሰራር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
ምንጭ: የግብርና ሚኒስቴር

Related Post