አርእስተ ዜና
Sat. Nov 23rd, 2024

በግብርና ኢንሹራንስ ተሞክሮዎች ላይ ውይይት ተካሄደ

በግብርና ኢንሹራንስ ተሞክሮዎች ላይ ውይይት ተካሄደ
በግብርና ኢንሹራንስ ተሞክሮዎች ላይ ውይይት ተካሄደ

ግብርና ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ያለው የግብርና የአስራ አምስት ዓመት የኢንሹራንስ ልምድ እና አለም አቀፍ የግብርና ኢንሹራንስ ተሞክሮዎችን የሚያስቃኙ ሰነዶች ላይ ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ፡፡

አፍሪካ ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ፣ በጎርፍ እና በድርቅ በመጎዳቷ ገፅታዋ እየተቀየረ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ዑመር ሁሴን መድረኩን ሲከፍቱ ተናግረዋል፡፡ የአየር ንብት ለውጥ በተለይ ለአፍሪካ የህልውና ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ የችግሩን አያያዝ መንገዶችን መፍጠር እንደሚያስፈልግ ገልፀው ለዚህም አንዱ አፋጣኝ እርምጃ የግብርና ኢንሹራንስ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ማንደፍሮ ንጉሴ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያለው የግብርና ኢንሹራንስ ላይ ያሉ ጠንካራ ጎኖች ፣ ተግዳሮቶች እና በቀጣይ እንዴት እንስራ የሚሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረግ የመድረኩ ዓለማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከመድረኩ ተሳታፊዎች የግብርና ኢንሹራንስን የተመለከቱ የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ተነስተው ወይይት ተደርጎባቸው የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

Related Post