አርእስተ ዜና
Sat. Nov 23rd, 2024

በ2014 የጀት ዓመት 19 ቢሊየን ብር በኦዲት ተገኘ

በ2014 የጀት ዓመት 19 ቢሊየን ብር በኦዲት ተገኘ
በ2014 የጀት ዓመት 19 ቢሊየን ብር በኦዲት ተገኘ

በተጠናቀቀው የ2014 በጀት ዓመት ከሶስቱም የኦዲት አይነቶች ከ19 ቢሊየን ብር በላይ ተወስኗል።

በገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ኦዲት ዳይሬክቶሬት በአዳማ ከተማ እያካሄደ በሚገኘው የ2014 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም እና የ2015 በጀት ዓመት ቀጣይ ዕቅድ ውይይት ላይ እንደተገለፀው ከዴስክ ኦዲት፣ ውስን ኦዲት እና አጠቃላይ ኦዲቶች በ2014 በጀት ዓመት 19.21 ቢሊየን ብር መወሰን እንደተቻለ ተነግሯል፡፡ ይህም የዕቅዱን 137 በመቶ ነው፡፡

የዳይሬክቶሬቱን የ2014 በጀት ዓመት እቅድ ያቀረቡት የታክስ ኦዲት ድጋፍና ክትትል የስራ ሂደት አቶ ዳኛቸው ጌትነት እንደገለፁት ባሳለፍነው በጀት ዓመት በሶስቱም የታክስ አይነቶች 7 ሺህ 95 ማህደሮችን ኦዲት ለማድረግ ታቅዶ 7 ሺህ 260 ማህደሮችን ኦዲት ማድረግ ተችሏል፡፡ ይህም የዕቅዱን 102.3 በመቶ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም በታክስ ዕዳ ዳይሬክቶሬት ከተሰበሰበው 36.38 ቢሊየን ብር ውስጥ 17.68 ቢሊየን ብር ወይም የዕቅዱን 48.6 በመቶ በታክስ ኦዲት የተሰበሰበ ነው፡፡

በተጨማሪም በ320 ማህደራት ላይ በተደረገ የታክስ ኦዲት 455.5 ሚሊየን ብር በቅድመ ግብር እንዲሁም ከ558 ማህደራት 748.17 ሚሊየን ብር የተጨማሪ እሴት ታክስ በድምሩ 1.2 ቢሊየን ብር ያልተገቡ ተመላሾችን ማስቀረት መቻሉን ገልፀዋል፡፡

Related Post