አርእስተ ዜና
Sat. Nov 23rd, 2024

ከንግድ ማጭበርበር ከ50 ቢሊየን ብር በላይ ማዳን ተቻለ

ከንግድ ማጭበርበር ከ50 ቢሊየን ብር በላይ ማዳን ተቻለ
ከንግድ ማጭበርበር ከ50 ቢሊየን ብር በላይ ማዳን ተቻለ

የጉምሩክ ኮሚሽን በ2014 በጀት ዓመት በንግድ ማጭበርበርና በኮንትሮባንድ መከላከል በሰራው ጠንካራ የቁጥጥር ስራ መንግስት ሊያጣው የነበረን 50ቢሊየን 46ሚሊየን 954ሺ 335ብር ከ57 ሳንቲም ማዳን መቻሉን የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች የተቋሙን የ2014 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም በገመገሙበት ወቅት ተገልጿል፡፡

ይህ አፈፃፀም ከ2013 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም የ13.3 ቢሊየን ብር ወይም 36.28 በመቶ ብልጫ እንዳለው በግምገማው ተጠቁሟል፡፡
ማዳን ከተቻለው ገንዘብ ውስጥም በኢንተለጀንስ ስራዎች 1.06 ቢሊየን፣በድንገተኛ ፍተሻ 843.82 ሚሊየን፣ በገቢ ኮንትሮባንድ ቁጥጥር 4.284 ቢሊየን፣ በወጭ ኮንትሮባንድ ቁጥጥር 836.64 ሚሊየን፣ከድህረእቃ አወጣጥ ኦዲት 9.465 ቢሊየን፣ የቀረጥ ነፃ መብት አጠቃቀምን በመቆጣጠር 530.81 ሚሊየን እና ቀሪው 33.02 ቢሊየን ብር በመደበኛ ፍተሻ ስራ ማዳን የተቻለ መሆኑንም ከግምገማው ማወቅ ተችሏል፡፡

በእቅድ ግምገማው ወቅት የገቢዎች ሚኒስትር ክቡር አቶ ላቀ አያሌው በንግድ ማጭበርበር እና ኮንትሮባንድ መከላከል ስራዎች ላይ ጉልህ ተሳትፎ ላደረጉ ለጉምሩክ ኮሚሽን አመራርና ስራተኞች፣ ለፌዴራል ፖሊስ አባላት፣ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት፣ ለብሔራዊ መረጃና ደህንነት አባላት እንዲሁም ለክልል የፀጥታ አካላትና ለመላው ህብረተሰብ ምስጋናቸውን አቅርበው በቀጣይም የተለመደው ትብብር እንዲቀጥል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Related Post