አርእስተ ዜና
Sat. Nov 23rd, 2024

ከ45 ቢሊየን ብር በላይ በኮንትሮባንድ እና ንግድ ማጭበርበር ተያዘ

ከ45 ቢሊየን ብር በላይ በኮንትሮባንድ እና ንግድ ማጭበርበር ተያዘ
ከ45 ቢሊየን ብር በላይ በኮንትሮባንድ እና ንግድ ማጭበርበር ተያዘ

የጉምሩክ ኮሚሽን ባለፉት 11 ወራት በሰራው የህግ ማስከበር ስራ በኮንትሮባንድ እና ንግድ ማጭበር ኢትዮጵያ ልታጣ የነበረውን 45 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ ማዳን መቻሉን አስታወቀ፡፡

የጸረ ኮንትሮባንድ እና ህገ-ወጥ ንግድን ለመከላከል የሚያስችል ግብረ ኃይል በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስተባባሪነት የውይይት መድረክ በሶማሌ ክልላዊ መንግስት ጅግጅጋ ከተማ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡

ግብረ ኃይሉም የፌደራል ጉሙሩክና የፌደራል ፖሊስ እንዲሁም ከጠቅላይ ሚንስትር የተወጣጡ በሱማሌ፣በጅግጅጋ፣በአፋር በተወጣጣ የኦፕሬሽን አመራር አፈፃፀሙን በሪፖርት ቀርቦ ገምግሟል።

በመድረኩ የተገኙት የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ ÷ኮሚሽኑ የህግ ተገዥነትን ለማረጋገጥ የተለያዩ ስልቶችን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ባለፉት 11 ወራት ብቻ 604 ሚሊየን ብር የወጪ እና 3 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር የገቢ በድምሩ ከ4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡

በአጠቃላይ ኮሚሽኑ ባለፉት 11 ወራት በሰራው የህግ ማስከበር ስራ በኮንትሮባንድ እና ንግድ ማጭበርበር ሀገር ልታጣው የነበረውን ከ45 ቢሊየን ብር በላይ ማዳን መቻሉን ነው የገለጹት፡፡

ባለፉት ሶስት ዓመታት ህገ-ወጥ ንግድን እና ኮንትሮባንድን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በርካታ ስራዎች መሰራታቸውንም ገልጸዋል፡፡ ችግሩ የአገር ደህንነት እና ስጋት ወደማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ በተቋማት መካከል ያለው ቅንጅታዊ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል ማለታቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የተጀመረው በክልል አመራር ያካተተ ቅንጅታዊ አሰራር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና በመዋቅር ላይ የሚነሱ ቅሬታዎች በውስጥ የተሰገሰጉትን ኔትዎርኮችን ተገቢውን ማጣራት በማድረግ እርምጃ እንደሚወስድና ከድንበር ንግድ ጋር ተያይዞ ለተነሳውም ጥያቄ በጥናት ላይ የመሰረተ ምላሽ እንደሚሰጥ የንግድና ቀጣናዊ ሚንስቴር ምኒስትር አቶ ገብረ መስቀል ጫላ በማጠቃለያቸው አንስተው በሱማሌ ክልል ህዝቦችና መንግስት ያሉት ጅምሮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አሳስበዋል።

Related Post