አርእስተ ዜና
Sat. Nov 23rd, 2024

ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን የኤሌክትሪክ ኃይል ልትሽጥ ነው ተባለ

ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን የኤሌክትሪክ ኃይል ልትሽጥ ነው ተባለ
ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን የኤሌክትሪክ ኃይል ልትሽጥ ነው ተባለ

ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ የሚያስችላት የመግባቢያ ሥምምነት ተፈራረመች።

ይህ የተገለጸው በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሲሆን፤ የመግባቢያ ሥምምነቱን በኢትዮጵያ በኩል የፈረሙት የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትር ዴኤታ ሲሆኑ በደቡብ ሱዳን በኩል የሀገሪቱ የውሃና ግድብ ሚኒስትር ዴኤታ ናቸው።

በሥምምነቱ መሰረት የጥናት ሥራዎች በአንድ ዓመት ውስጥ እንዲጠናቀቁ የታሰበ ሲሆን ግንባታውንም ከጥናቱ በኋላ ባሉት በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት በማጠናቀቅ የኃይል ሽያጭ ስምምነቱ ተግባራዊ ይሆናል።

ሀገራቱ የተፈራረሙት የኃይል ሽያጭ ስምምነት በአጭር ጊዜ ውስጥ 357 ኪሎ ሜትር የሚረዝም ባለ 230 ኪሎ ቮልት መስመር ከጋምቤላ 2 ማከፋፈያ ጣቢያ ወደ ደቡብ ሱዳን ማላካል ግዛት መስመር መዘርጋትን ያካትታል።

በረጅም ጊዜ ደግሞ እስከ 700 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ባለ 400 ወይም 500 ኪሎ ቮልት መስመር ከቴፒ ወደ ቦር ጁባ መዘትጋትን ታሳቢ አድርጓል። ሀገራቱ በቀጣይ ለሚሰሯቸው ሥራዎች ጥምር ቴክኒካል ኮሚቴ አዋቅረው ወደስራ እንደሚገቡ በስምምነቱ ላይ ተጠቅሷል።

Related Post