አርእስተ ዜና
Thu. Dec 26th, 2024

የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 701 ደረሰ

የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 701 ደረሰ
የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 701 ደረሰ

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3410 የላብራቶሪ ምርመራ አርባ ስድስት (46) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሰባት መቶ አንድ (701) ደርሷል፡፡

በተያያዘ ዜና በጋምቤላ በቀን 180 ናሙናዎችን መመርመር የሚያስችል የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ ማሽን ስራ ጀመረ፡፡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ እንዳሉት በሀገሪቱ ኮቪድ-19 መከሰቱ ከታወቀ ጀምሮ በጋምቤላ ክልል በርካታ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ ሲከናወን ቆይቷል ብለዋል፡፡

በክልሉ በርካታ የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙና ከደቡብ ሱዳን ጋርም በሰፊው የሚዋሰን ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ኮሮናቫይረስን ለመመርመር የሚያስችል ማሽን ስራ እንዲጀምር ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ መቆየተቱንም አብራርተዋል፡፡

የክልሉ መንግስት የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከልና ለመቆጣጠር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው በተለያዩ ቦታዎች በሚደረገው ሙቀት ልየታ ህብረተሰቡ ያለምንም ፍራቻ ምርመራ ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ካን ጋትሉዋክ በበኩላቸው የክልሉ መንግስት ከጤና ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመነጋገር በክልሉ ቀደም ሲል ለኤች አይ ቪ መመርመሪያ ያገለግል የነበረው ማሽን አዲስ ሶፍት ዌር በመጫን ለኮቪድ-19 ምርመራ እንዲውል መደረጉን አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ናሙናዎችን ወደ አዲስ አበባ በመላክ ውጤቶችን ሲገልፁ እንደነበር ጠቅሰው በክልሉ ምርመራ መጀመሩ ጊዜንና ወጪን ከመቆጠብ በተጨማሪ በክልሉ በተለያዩ ለይቶ ማቆያዎች ለሚገኙ ዜጎች በቅርበት አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡

በጋምቤላ በቀን 180 ናሙናዎችን መመርመር የሚያስችል የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ ማሽን ስራ ጀመረ
በጋምቤላ በቀን 180 ናሙናዎችን መመርመር የሚያስችል የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ ማሽን ስራ ጀመረ

በክልሉ ስራ የጀመረው የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ ማሽን በቀን እስከ 180 ናሙናዎችን የመመርመር አቅም እንዳለው የጠቀሱት አቶ ካን ምርመራው ከተጀመረ ወዲህ ሰባት ናሙናዎች ተመርምረው ሁሉም ውጤታቸው ኔገቲቭ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ከስደተኞች ጋር ተያይዞ ሊከሰት የሚችለውን የቫይረሱን ወረርሽኝ ለመመርመር የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ በክልሉ ከሚገኙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመነጋገር ላይ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡

Related Post