አርእስተ ዜና
Sat. Nov 23rd, 2024

ላይቭ ኤንድ ክሎዝ አፕ የመጀመሪያውን ኮንሰርት አዘጋጀ

ላይቭ ኤንድ ክሎዝ አፕ የመጀመሪያውን ኮንሰርት አዘጋጀ
ላይቭ ኤንድ ክሎዝ አፕ የመጀመሪያውን ኮንሰርት አዘጋጀ

ላይቭ ኤንድ ክሎዝ አፕ (ሙዚቃዊ) የመጀመሪያውን ኮንሰርት ያዘጋጀ ሲሆን ታዋቂው ሙዚቀኛና አቀናባሪ ጆርጋ መስፍን የዚህኛውን ክፍል ላይቭና ክሎዝአፕ ፕሮዲውስ ያደረገው ሲሆን ኪሩቤል ተስፋዬ፣ ሄኖክ ተመስገን፣ ግሩም መዝሙርና ቴዎድሮስ አሰፋ ያሉ ትልልቅ ሙዚቀኞች ተሳትፈውበታል፡፡

በመጋቢት 29 2014 ዓ.ም. አራት ሙዚቃዎችን የያዘው የመጀመሪያውን ኮንሰርት በእሱባለው ይታየው (የሺ) የሚጀመር ሲሆን በቀጣይም የሰባት አርቲስት ስራዎች በየወሩ ይቀርባሉ፡፡



የላይቭ ኤንድ ክሎዝ አፕ ሀሳብ የተጠነሰሰው ከሁለት አመት በፊት ኮቪድ 19 በሀገራችን በመከሰቱና እንደቀድሞው በአካል የሙዘቃ ኮንስርቶችን ማዘጋጀት ባለመቻሉ ሙዚቃን የሚወደው የህብረተሰብ ክፍል ባለበት ሁኖ በዲጂታል ሚዲያው መስኮት ኮንሰርት እንዲደርሰው በማሰብ እንዲሁም የወረርሺኙ መከሰት ሴክተሩንም ሆነ የባለሙያውን ችግር በጥቂቱም ቢሆን ለመፍታት በማሰብ ነው፡፡

በግዜ ሂደት ላይቭ ኤንድ ክሎዝ አፕ የአርቲስቱንና የሙዚቃ ተመልካቹን ግንኙነት እያጠናከረ በመምጣቱ የሙዚቃዊ አንድ ብራንድ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ በመሆኑም ከዚህ ቀደም ሁለት የተሳኩ ስራዎች በዚሁ መደረክ የቀረቡ ሲሆን በአዲስ አቀራረብና ጥራት ሰባት ኮንሰርቶችን የያዘውንና ሶስተኛውን ክፍል ይዘን መጥቷል፡

ላይቭ ኤንድ ክሎዝ አፕ ለኢትዮጵያውያን ሙዚቃ ወዳጆች ብቻ ሳይሆን ለዓለም ማህበረሰብ በሩ ክፍት ነው፡፡ በዚሁ አጋጣሚም በ ላይቭ ኤንድ ክሎዝ አፕ ቀጣይ መድረኮች ላይ በአጋርነት እንድንስራም እንጋብዛለን።

ሙዚቃዊ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ኢንደስትሪ ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚሰራ ድርጅት ነው፡፡ ሙዚቃዊ የተቋቋመው በሙዚቃ ኢንዱስትሪው በኢትዮጵያ ካካበተው የ17 አመታት የስራ ልምድና የ25 ዓመታት የዓለምአቀፍ ተሞክሮ መሰረት ሲሆን እ.ኤ.አ በ2022 አስራ ስድሰት ሙዚቀኞችን እና ከመቶ በላይ የሙዚቃ ስራዎች በመላው አለም ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡

Related Post