አርእስተ ዜና
Sat. Nov 23rd, 2024

የቀጣዩ አመት ምገባ መርሀግብር 600 ሺህ ተማሪዎችን ያካትታል

የቀጣዩ አመት ምገባ መርሀግብር 600 ሺህ ተማሪዎችን ያካትታል
የቀጣዩ አመት ምገባ መርሀግብር 600 ሺህ ተማሪዎችን ያካትታል

የቀጣዩ አመት የተማሪዎች ምገባ መርሀግብር 600 ሺህ ተማሪዎችን ያካትታል ሲሉ ኢ/ር ታከለ ኡማ አመልክተዋል።

በዘንድሮው አመት ለተማሪዎች የተደረገው ድጋፍ በቀጣዩ አመት በጥራትም በቁጥርም ተጠናክሮ የሚቀጥል ተብሏል። የቀጣዩ አመት የምገባ መርሀግብር 600 ሺህ ተማሪዎችን ያካትታል ሲሉ ኢ/ር ታከለ ኡማ ገለጹ።

በቴሌቪዥን እየተሰጠ ባለው “ትምህርት በቤቴ“ መርሀግብር በአጭር የፅሁፍ መልእክት ለተሳተፉና ጥሩ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ሽልማቱ የተበረከተላቸው በተለያየ የትምህርት ደረጃ ላይ የሚገኙ 41 ተማሪዎች ናቸው።

ለተሸላሚ ተማሪዎች የላፕቶፕ ስጦታ የተበረከተ ሲሆን ልጆቻቸውን በጥንካሬ ለደገፉ ወላጆችም የቴሌቪዥን ስጦታ ተበርክቶላቸዋል። ሽልማቱን ያበረከቱት ኢ/ር ታከለ ኡማ በኮሮና ቫይረስ ምክኒያት መደበኛ የመማር ማስተማሩ ሂደት ቢስተጓጎልም ቴክኖሎጂን በተከተለና ተማሪዎችንም ባሳተፈ መልኩ የመማር ማስተማሩ መቀጠል ተችሏል ብለዋል።

በተማሪዎች ላይ የሚደረገው ኢንቨስትመንት ትውልድ መገንባት እንደመሆኑ ከጥቅሙ አንፃር ወጪው አነስተኛ ነው ብለዋል ኢ/ር ታከለ ኡማ። የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ላይ የሰጠው ተረኩረት ቀጣይ ነው ብለዋል። በተያዘው አመት ለተማሪዎች የተደረገው የዩኒፎርም፣የደብተር፣መማሪያ ቁሳቁስና የምገባ መርሀግብር በቀጣዩ አመት በጥራትም በቁጥርም ጨምሮ ይቀጥላል ብለዋል ኢ/ር ታከለ።

በተያዘው አመት ለ300ሺህ ተማሪዎች እየተደረገ ያለው “የተማሪዎች ምገባ መርሀግብር” በቀጣዩ አመት 600 ሺህ ተማሪዎች የሚካተቱበት ይሆናል ሲሉ ኢ/ር ታከለ ኡማ ተናግረዋል።

በአፍሪሄልዝ ቴሌቪዥንና በአዲስ አበባ ት/ት ቢሮ በትብብር እየተሰራጨ ያለው “ትምህርት በቤቴ” መርሀግብር ከጠዋቱ 3 ሰአት እስከ ቀኑ 9:30 መተላለፉን የሚቀጥል ይሆናል።

Related Post