አርእስተ ዜና
Sat. Nov 23rd, 2024

ኢትዮጵያ ሁለት የቴሌኮሙኒኬሽን ፈቃዶችን ለመስጠት መጠየቂያ አወጣች

ኢትዮጵያ ሁለት የቴሌኮሙኒኬሽን ፈቃዶችን ለመስጠት መጠየቂያ አወጣች
ኢትዮጵያ ሁለት የቴሌኮሙኒኬሽን ፈቃዶችን ለመስጠት መጠየቂያ አወጣች

ኢትዮጵያ ሁለት የቴሌኮሙኒኬሽን ፈቃዶችን ለመስጠት መጠየቂያ አወጣች። የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን በዛሬው እለት ሁለት የቴሌኮሙኒኬሽን ፈቃዶችን ለመስጠት የፍላጎት መግለጫ መጠየቂያ አውጥቷል።

ባለሥልጣኑ የፈቃድ አሠጣጥ ሂደቱን በኮሙኒኬሽን አገልግሎት አዋጅ በተሠጠው ሥልጣን መሠረት እየመራ ሲሆን ይህም የኢትዮጵያን የቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ ለግሉ ዘርፍ የመክፈት ሂደት ዋናው አካል መሆኑን በላከው መግለጫ አስታውቋል።

ኢትዮ ቴሌኮም ይዞ ከሚገኘው ፈቃድ በተጨማሪ ሁለት ፈቃዶችን በቴሌኮሙኒኬሽን ሥራ ላይ ለተሠማሩ ኩባንያዎች የመሥጠት ሂደት መንግሥት በዘርፉ ውድድርን ለመፍጠር ካቀዳቸው የአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳዎች አንዱ መሆኑንም ጠቅሷል።

በዚህም የመንግሥት ዋና ዋና ዓላማዎች የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎቶችን ተደራሽነትና ቀልጣፋነት ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚውን ለውጥ ለማፋጠን የሚያስፈልገውን የአገልግሎት ጥራትና ውጤታማነት በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ እና ከዲጂታል ኢኮኖሚ የሚገኘውን ጥቅም የበለጠ ለማስፋት መሆኑንም ባለስልጣኑ አስታውቋል።

በዚህም መሰረት ሁለት ሀገር አቀፍ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎቶችን ለመስጠት የሚያስችሉ ፈቃዶች መስፈርቶችን ለሚያሟሉ የቴሌኮሙኒኬሽ ኩባንያዎች በኮሙኒኬሽን አገልግሎት አዋጅ ቁጥር 1148/2011 መሠረት በውድድር ላይ በተመሠረት ግልፅ ጨረታ የሚሰጡ መሆኑን ጠቅሷል።

Related Post