አርእስተ ዜና
Sat. Nov 23rd, 2024

የዲጂታል ግብርና ኢኖቬሽን ማዕከል ምስረታ ላይ ምክክር ተካሄደ

የዲጂታል ግብርና ኢኖቬሽን ማዕከል ምስረታ ላይ ምክክር ተካሄደ
የዲጂታል ግብርና ኢኖቬሽን ማዕከል ምስረታ ላይ ምክክር ተካሄደ

የግብርና ሚኒስቴርና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተውጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎችና ኃላፊዎች በተገኙበት የዲጂታል ግብርና ኢኖቬሽን ማዕከል በአገር ደረጃ መመስረት በሚያስችሉ ነጥቦች ላይ ምክክር ተካሄደ፡፡

በምክክር መድረኩ የተገኙት በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ኤክስቴንሽን ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ገርማሜ ጋሩማ እንደገለፁት የምክክር መድረኩ ዋና አላማ የሚመሰረተውን ፕሮጀክት ለዋና ዋና ባለድርሻ አካላት ማስተዋወቅ ነው፡፡



የኢኖቬሽኑ አለም አቀፍ የአጋሮችና ባለድርሻ አካላት የዲጂታል ግብርና ኢኖቬሽን ማዕከል እንደ አገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ለመመስረትና ለስኬታማ አፈጻጸሙ ወሳኝ መሆኑንም ጠቅሰው ማዕከሉ ለአገራችንና ከዛም በላይ ሰፊ ጥቅም ስለሚሰጥ እያንዳንዱ ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅበትን አስተዋፅኦ ማበርከት እንዳለበት ተናግረዋል፡ በማለት የግብርና ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ የዲጂታል ግብርና ኢኖቬሽን ስራዎች ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታና የረቂቅ ኢኖቬሽኑን አመታዊ የስራ እቅድ መገምገምና ማፅደቅ ለፕሮጀክቱ ዝግጅትና ትግበራ ሚናው የጎላ እንደሆነም አቶ ገርማሜ አብራርተዋል፡፡ በመሆኑም ይህ እድል ለግብርና ሚኒስቴር ከዚህ በፊት የግብርና ኤክስቴንሽን ምክረ ሃሳብ አገልግሎት መስጫ ስርዓትን በተመለከተ የተጀመሩ ስራዎችን ለማሳደግ ያስችላል ብለዋል፡፡

በምክክር መድረኩ ለፕሮጀክቱ ምስረታ ግብዓት የሚሆኑ የግብርና ኤክስቴንሽንና ምክረ ሃሳብ ዲጂታላይዜሽን፤ ዲጂታል ግሪን፤ ዲጂታል ኢኖቬሽንና ፋርም ሬዲዮ በሚሉ ነጥቦች ላይ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ በውይይቱ ገንቢ የሆኑ ግብዓቶች የተነሱ ሲሆን አዲሱ ፕሮጀክት ከዲጂታል ኤክስቴንሽንና ምክረ ሀሳብ አገልግሎት ጋር ተስማሚ እንደሆነ ከተሳታፊዎች ተነስቷል፡፡



በተለይም የዲጂታል ኤስቴንሽንና ምክረ ሃሳብ ትኩረቱ በተለያዩ ስራዎች ማለትም በስርዓተ ምግብ፤ በአሲዳማ አፈር እነዲሁም በድህረ ምርት አያያዝ ላይ አነስተኛ አርሶ አደሮችን በተለይም ሴቶችንና ወጣቶችን ለመደገፍ እየሰራ ሲሆን ይህም ለአዲሱ ፕሮጀክት የራሱን ግብዓት አበርክቷል፡፡

Related Post