አርእስተ ዜና
Fri. Sep 20th, 2024

ኤጀንሲው የሳይበር ጥቃቶችን የመከላከል አቅሙ 96 በመቶ ደርሷል

ኤጀንሲው የሳይበር ጥቃቶችን የመከላከል አቅሙ 96 በመቶ ደርሷል
ኤጀንሲው የሳይበር ጥቃቶችን የመከላከል አቅሙ 96 በመቶ ደርሷል

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በተያዘው የበጀት አመቱ ስድስት ወራት ውስጥ የሳይበር ደህንነት ጥቃትን የመከላከል አቅሙ ከ85 በመቶ ወደ 96 በመቶ በላይ መድረሱን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ገለጹ።

ዋና ዳይሬክተሩ የስድስት ወር የኤጀንሲውን የስራ አፈጻጸም አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል። የኤጀንሲው የሳይበር ጥቃቶችን ቅድመ መከላከል፣ ጥቃት የደረሰባቸውን መልሶ ወደ ነበሩበት ስራ የመመለስ አቅሙ አድጓል ብለዋል።



ባለፉት ስድስት ወራት ከ3 ሺ 400 በላይ የሳይበር ጥቃት ሙኩራ ተደርጓል ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ። ባለፉት ጊዜያት በባንኮች፣ በማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት፣ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ በክልል ቢሮዎች፣ የትምህርት ተቋማት፣ የሚዲያ ተቋማትና መሰል ተቋማት የሳይበር ጥቃት ኢላማ ተደርገው እንደነበር ገልጸዋል።

እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ፣ በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ከፍተኛ የሳይበር ጥቃት ሙከራ ተደርጎ የነበረ ቢሆንም ጉዳቱን ማስቀረት መቻሉ ተገልጿል፡፡

ምንጭ – ኢቢሲ

Related Post